ተወዳዳሪ ፡ የለህም (Tewedadari Yelehem) - አስቴር ፡ ዮሴፍ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስቴር ፡ ዮሴፍ
(Aster Yosef)

Aster Yosef 3.jpg


(3)

አንተው ፡ ትሻለኛለህ
(Antew Teshalegnaleh)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:02
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ ዮሴፍ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Yosef)

አዝ፦ አቻና ፡ ተወዳዳሪ ፡ የለህም
ብቻህን ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፫x)

እንዴት ፡ እንዳቆምካት ፡ ምድርና ፡ መሰረቷን
በምን ፡ እንዳፀናሃት ፡ የድንጋይ ፡ ማእዘኗን
ብቻህን ፡ ጌታ ፡ ነህ (፬x)
የባሕር ፡ ዳር ፡ ድንበሩን ፡ ለአንተ ፡ ማን ፡ አሳየህ
ሁሉ ፡ በቃልህ ፡ ሆነ ፡ ሰምቶህ ፡ እየታዘዘህ
(፪x)

አዝ፦ አቻና ፡ ተወዳዳሪ ፡ የለህም
ብቻህን ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፫x)

ከአህዛብ ፡ ጥበበኞች ፡ የሚመስልህ ፡ ማን ፡ አለ
ከመንግሥታቸውም ፡ ውስጥ ፡ ተወዳዳሪ ፡ የለህ
ብቻህን ፡ ጌታ ፡ ነህ (፬x)
ሁሉም ፡ ፍጥረት ፡ በፊትህ ፡ ለአንተ ፡ ይንበረከካሉ
ወደዱም ፡ ጠሉም ፡ ለክብርህ ፡ ወድቀው ፡ ይሰግዳሉ
(፪x)

አዝ፦ አቻና ፡ ተወዳዳሪ ፡ የለህም
ብቻህን ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፫x)

ይሄ ፡ የሰማነው ፡ ምንኛ ፡ እጅግ ፡ ጥቂት ፡ ነው
የኃይሉንስ ፡ ነጐድጓድ ፡ የሚያስተውለው ፡ ማነው
ብቻውን ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው (፬x)
ትልቅ ፡ ነው ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሃሳቡን ፡ የሚያውቅ ፡ ማነው
በሠማይም ፡ በምድር ፡ እኩያ ፡ አቻ ፡ የሌለው
(፪x)

አዝ፦ አቻና ፡ ተወዳዳሪ ፡ የለህም
ብቻህን ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፫x)

ብቻህን ፡ ጌታ ፡ ነህ (፬x)