ተመስገን (Temesgen) - አስቴር ፡ ዮሴፍ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስቴር ፡ ዮሴፍ
(Aster Yosef)

Aster Yosef 3.jpg


(3)

አንተው ፡ ትሻለኛለህ
(Antew Teshalegnaleh)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:23
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ ዮሴፍ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Yosef)

ተመሥገን (፲x)

ከአብ ፡ ዘንድ ፡ ያለኸኝ ፡ ለእኔ ፡ ጠበቃዬ
በፍቅር ፡ የምታየኝ ፡ ወዳጅ ፡ አፍቃሪዬ
ፈልጌ ፡ የማላጣህ ፡ የምትቆም ፡ ከጐኔ
አንተ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ፡ ድጋፍ ፡ መከታዬ (፪x)

ልዩ ፡ ወዳጄ ፡ ነህ ፡ ቋሚ ፡ ተጠሪዬ
ለሚደርስብኝም ፡ ነህ ፡ ተቆርቋሪዬ
ከእኔ ፡ የማትለይ ፡ የማትጠፋ ፡ ከጐኔ
አንተ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ፡ ተሟጋች ፡ ለነፍሴ (፪x)

ተመሥገን (፲x)

ከገመትኩት ፡ በላይ ፡ ፍቅሩ ፡ ለእኔ ፡ በዛ
ፍፁም ፡ አይገመት ፡ እንዲህ ፡ እንደ ፡ ዋዛ
ግርዶሼን ፡ ቀደደው ፡ ልጁን ፡ አድርጐ ፡ ቤዛ
እግዚአብሔር ፡ ወደደኝ ፡ በፍቅሩ ፡ እኔን ፡ ገዛ (፪x)

ፍቅሩ ፡ እጅግ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ከሁሉም ፡ የሚስብ
ያየ ፡ የሰማውን ፡ እጅግ ፡ የሚያስደንቅ
በከበረው ፡ ዙፋን ፡ ነፍሴን ፡ አኖረልኝ
ሁሉንም ፡ ድል ፡ አድርጐ ፡ ድል ፡ አወጀልኝ (፪x)

ተመሥገን (፲x)

መላእክት ፡ ተደፍተው ፡ ለሚሰግዱልህ
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ብለው ፡ ለሚያዜሙልህ
እኔም ፡ ተነስቼ ፡ ቅዱስ ፡ ነህ ፡ እላለሁ
ከእግርህ ፡ ሥር ፡ ወድቄ ፡ ክብርን ፡ እሰጣለሁ (፪x)

በዕልልታ ፡ ሽብሸባ ፡ ቤትህ ፡ እገባለሁ
ሁሌም ፡ አምላኬ ፡ ነህ ፡ እገዛልሃለሁ
ለአንተ ፡ የሚሳንህ ፡ አላየሁምና
ዛሬም ፡ እልሃለሁ ፡ ይብዛልህ ፡ ምሥጋና
ዛሬም ፡ ነገም ፡ ለአንተ ፡ ይብዛልህ ፡ ምሥጋና (፪x)

ተመሥገን (፲x)