ነፍሱን (Nefsun) - አስቴር ፡ ዮሴፍ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስቴር ፡ ዮሴፍ
(Aster Yosef)

Aster Yosef 3.jpg


(3)

አንተው ፡ ትሻለኛለህ
(Antew Teshalegnaleh)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 6:38
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ ዮሴፍ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Yosef)

ነፍሱን ፡ እስከ ፡ መስጠት ፡ ወደደኝ
የፍቅሩ ፡ ምርኮኛ ፡ አደረገኝ
ሳይዋጋ ፡ እኔን ፡ ማረከኝ
ሳይታገል ፡ ፍቅሩ ፡ አሸነፈኝ (፪x)

እኔም ፡ በተራዬ ፡ እንዳቅሜ
ምላሼ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ወዳጄ
ደስ ፡ ካለህ ፡ ውዴ ፡ መውደዴ
ይኸው ፡ እገልፃለሁ ፡ ማፍቀሬን
ያለኝን ፡ ክብሬን ፡ እጥላለሁ
ከእግርህ ፡ ሥር ፡ ወድቄ ፡ እሰግዳለሁ
የነፍሴ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ
በፊትህ ፡ ልስበረው ፡ ጠርሙሴን
ከእግርህ ፡ ስር ፡ ይፍሰስ ፡ ሽቶዬ
ፍቅሬን ፡ መግለጫ ፡ ነው ፡ ጌታዬ (፪x)

መውደዴን ፡ እገልፃለሁ ፡ መውደዴን (፬x)
እወድሃለሁ (፰x)

አጥፊዬ ፡ ተነስቶ ፡ ሊያጠፋኝ
የሞት ፡ ጣር ፡ ይዞ ፡ ሲያስፈራራኝ
ጠላቴም ፡ ሞትን ፡ ሲመኝልኝ
አንተ ፡ ነህ ፡ ሕይወት ፡ ያወጅክልኝ
አጥፊዬ ፡ ተነስቶ ፡ ሊያጠፋኝ
የሞት ፡ ጣር ፡ ይዞ ፡ ሲያስፈራራኝ
ጠላቴም ፡ ሞትን ፡ ሲመኝልኝ
አንተ ፡ ግን ፡ በቅን ፡ ፈረድክልኝ

እኔም ፡ በተራዬ ፡ እንዳቅሜ
ምላሼ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ወዳጄ
ደስ ፡ ካለህ ፡ ውዴ ፡ መውደዴ
ይኸው ፡ እገልፃለሁ ፡ ማፍቀሬን
ያለኝን ፡ ክብሬን ፡ እጥላለሁ
ከእግርህ ፡ ሥር ፡ ወድቄ ፡ እሰግዳለሁ
የነፍሴ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ
በፊትህ ፡ ልስበረው ፡ ጠርሙሴን
ከእግርህ ፡ ስር ፡ ይፍሰስ ፡ ሽቶዬ
ፍቅሬን ፡ መግለጫ ፡ ነው ፡ ጌታዬ (፪x)

መውደዴን ፡ እገልፃለሁ ፡ መውደዴን (፬x)
እወድሃለሁ (፰x)

ለዘለዓለም ፡ ለአንተ ፡ ታጨኹኝ
በፍቅሩ ፡ ጥልቀት ፡ ተወደድኩኝ
ንጉሤን ፡ ውበቴን ፡ ወደሃል
ላትተወኝ ፡ ቃል ፡ ገብተህልኛል (፪x)

እወድሃለሁ (፰x)