From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ምን ፡ ይሳንሃል ፡ ምን ፡ ያቅትሃል
ሁሉ ፡ ይቻልሃል ፡ ሁሉ ፡ ይቻልሃል
ምን ፡ ይሳንሃል ፡ ምን ፡ ያቅትሃል
ሁሉ ፡ ይቻልሃል ፡ ሁሉ ፡ ይቻልሃል
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ለአንተ ፡ ምን ፡ ይሳንሃል
ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ለአንተ ፡ ምን ፡ ያቅትሃል (፪x)
የእስራኤልን ፡ ሕዝብ ፡ ከባርነት ፡ ምድር
በውኑ ፡ ሊያወጣ ፡ ሙሴ ፡ ማን ፡ ነበር
አፌን ፡ በአፍህ ፡ ላይ ፡ አደርጋለሁ ፡ ብለህ
ላክኸው ፡ ወደ ፡ ፈርዖን ፡ ኮልታፋውን ፡ መርጠህ
በችሎታህ ፡ ታምነህ ፡ ይህን ፡ ትሰራለህ
ይህን ፡ ታደርጋለህ (፪x)
አዝ፦ ምን ፡ ይሳንሃል ፡ ምን ፡ ያቅትሃል
ሁሉ ፡ ይቻልሃል ፡ ሁሉ ፡ ይቻልሃል
ምን ፡ ይሳንሃል ፡ ምን ፡ ያቅትሃል
ሁሉ ፡ ይቻልሃል ፡ ሁሉ ፡ ይቻልሃል
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ለአንተ ፡ ምን ፡ ይሳንሃል
ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ለአንተ ፡ ምን ፡ ያቅትሃል (፪x)
ብዙ ፡ የተማሩ ፡ አዋቂዎችን ፡ ትተህ
ዓሣ ፡ አጥማጆችን ፡ ለራስህ ፡ መረጥህ
እጅግ ፡ ታናናሾች ፡ ተራ ፡ በተባሉት
ዓለምን ፡ አዳረስክ ፡ በወንጌልህ ፡ እሳት
በችሎታህ ፡ ታምነህ ፡ ይህን ፡ ትሰራለህ
ይህን ፡ ታደርጋለህ (፪x)
አዝ፦ ምን ፡ ይሳንሃል ፡ ምን ፡ ያቅትሃል
ሁሉ ፡ ይቻልሃል ፡ ሁሉ ፡ ይቻልሃል
ምን ፡ ይሳንሃል ፡ ምን ፡ ያቅትሃል
ሁሉ ፡ ይቻልሃል ፡ ሁሉ ፡ ይቻልሃል
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ለአንተ ፡ ምን ፡ ይሳንሃል
ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ለአንተ ፡ ምን ፡ ያቅትሃል (፪x)
ልባቸው ፡ ሲቀልጥ ፡ በዮርዳኖስ ፡ ሙላት
ታቦት ፡ ተሸክሙ ፡ እነዚያ ፡ ካህናት
በተንጣለለው ፡ ወንዝ ፡ ሰገባ ፡ እግራቸው
ለሁለት ፡ ከፍለህ ፡ አንተ ፡ አሻገርካቸው
በችሎታህ ፡ ታምነህ ፡ ይህን ፡ ትሰራለህ
ይህን ፡ ታደርጋለህ (፪x)
አዝ፦ ምን ፡ ይሳንሃል ፡ ምን ፡ ያቅትሃል
ሁሉ ፡ ይቻልሃል ፡ ሁሉ ፡ ይቻልሃል
ምን ፡ ይሳንሃል ፡ ምን ፡ ያቅትሃል
ሁሉ ፡ ይቻልሃል ፡ ሁሉ ፡ ይቻልሃል
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ለአንተ ፡ ምን ፡ ይሳንሃል
ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ለአንተ ፡ ምን ፡ ያቅትሃል (፪x)
ለመሞት ፡ ጥቂት ፡ ቀን ፡ የቀራትን ፡ አይተህ
እንድትመግበው ፡ ደሃዪቱን ፡ አዘህ
ከኮራት ፡ ፈፋ ፡ ውስጥ ፡ ጌታ ፡ አውጥተኸው
በሰራፍታ ፡ ምድር ፡ ኤሊያስን ፡ መገብኸው
በችሎታህ ፡ ታምነህ ፡ ይህን ፡ ትሰራለህ
ይህን ፡ ታደርጋለህ (፪x)
|