ከፍ ፡ በል (Kef Bel) - አስቴር ፡ ዮሴፍ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስቴር ፡ ዮሴፍ
(Aster Yosef)

Aster Yosef 3.jpg


(3)

አንተው ፡ ትሻለኛለህ
(Antew Teshalegnaleh)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 6:02
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ ዮሴፍ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Yosef)

አዝከፍ ፡ በል (፬x)
በምሥጋና ፡ ከፍ ፡ በል ፡ በዝማሬ ፡ ከፍ ፡ በል
በምሥጋና ፡ ከፍ ፡ በል ፡ በዝማሬ ፡ ከፍ ፡ በል
ከፍ ፡ ካለው ፡ በላይ ፡ ከፍ ፡ ላልከው
ለአንተ ፡ ምሥጋናን ፡ እሰጣለሁ
(፪x)

ሥምህን ፡ ጠርቼ ፡ አላፈርኩምና
ድንቅህ ፡ ለሕይወቴ ፡ ብዙ ፡ ነውና
ፊትህ ፡ ወድቄ ፡ ላቅርብ ፡ ምሥጋናዬን
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ላርግህ ፡ ባለውለታዬ

ከፍ ፡ በል (፬x)
በምሥጋና ፡ ከፍ ፡ በል ፡ በዝማሬ ፡ ከፍ ፡ በል
በምሥጋና ፡ ከፍ ፡ በል ፡ በዝማሬ ፡ ከፍ ፡ በል
ከፍ ፡ ካለው ፡ በላይ ፡ ከፍ ፡ ላልከው
ለአንተ ፡ ምሥጋናን ፡ እሰጣለሁ
(፪x)

ጠላት ፡ ሊይዘኝ ፡ ከኋላዬ ፡ መጥቶ
ባህሩም ፡ ሲናወጥ ፡ እስከ ፡ አፉ ፡ ሞልቶ
በዘረጋሁ ፡ ጊዜ ፡ በትሬን ፡ በእምነት
በድል ፡ ተሻገርኩ ፡ ሰጠመ ፡ ጠላት
አምላኬ ፡ ነህ ፡ አምላኬ (፮x)

አይቻለሁ ፡ ማዳንህን
አይቻለሁ ፡ ጥበቃህን
አይቻለሁ ፡ ችሎታህን
አይቻለሁ ፡ ብርታትህን
አይቻለሁ ፡ ምህረትህን
አይቻለሁ ፡ ያን ፡ ፍቅርህን
አይቻለሁ ፡ ጉልበትህን
አይቻለሁ ፡ ስልጣንህን

እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አለ (፪x)
እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለ ፡ እስኪ ፡ ማን ፡ አየ (፪x)
ይናገር ፡ ማን ፡ አየ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አየ
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም
እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም
(፪x)

አንተን ፡ ማን ፡ ይመስላል ፡ በዘመናት ፡ መሃል
ከአንተስ ፡ ጋር ፡ እግዚአብሔር ፡ ማን ፡ ይወዳደራል
የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ የኃይላን ፡ ኃያል
ገናናው ፡ እግዚአብሔር ፡ አንተን ፡ ማን ፡ ይመስላል

እንደ ፡ አንተ ፡ ያለ ፡ የለም (፪x)
እንደ ፡ አንተ ፡ ያለ ፡ የለም ፡ ለዘለዓለም (፪x)