From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
እነዚያስ ፡ ያንን ፡ የተማመኑበት
ተሰነካከለ ፡ ተስፋ ፡ ያደረጉበት
ክብራቸው ፡ ወደቀ ፡ ቀንዳቸው ፡ ተመታ
በዙፋኑ ፡ ከብሮ ፡ አለ ፡የእኛ ፡ ጌታ
ብቻህን ፡ ተዐምራት ፡ ያደረግህ ፡ ጌታ
ፍፁም ፡ የማትረታ
አዝ፦ በሠማይ ፡ በምድር ፡ ከቶ ፡ የለህ ፡ አቻ
ክበር ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ንገሥ ፡ አንተ ፡ ብቻ
ሠማይን ፡ እንደ ፡ መጋረጃ ፡ ዘርግቶ
እልፍኙን ፡ በውኃ አሳምሮ ፡ ሰርቶ
ምንም ፡ የሌለበት ፡ እጅግ ፡ ከደረቀ
አለቱን ፡ ሰንጥቆ ፡ ውሃን ፡ አፈለቀ (፪x)
አዝ፦ በሠማይ ፡ በምድር ፡ ከቶ ፡ የለህ ፡ አቻ
ክበር ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ንገሥ ፡ አንተ ፡ ብቻ
ሸለቆን ፡ የሚሞላ ፡ ተራራን ፡ የሚንድ
አገልጋዩን ፡ እንደ ፡ ነበልባል ፡ የሚያነድ
በተራሮች ፡ ላይ ፡ ውሆችን ፡ የሚያቆም
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ታላቅ ፡ አምላክ ፡ የለም
አዝ፦ በሠማይ ፡ በምድር ፡ ከቶ ፡ የለህ ፡ አቻ
ክበር ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ንገሥ ፡ አንተ ፡ ብቻ
በሚንበለበለው ፡ እሳት ፡ ውስጥ ፡ ቢከተን
የምታምኑት ፡ አምላክ ፡ ያድናችሁ ፡ ቢለን
የምናምነው ፡ አምላክ ፡ ዝም ፡ ብሎ ፡ አያየን
ነጥቆ ፡ ያወጣናል ፡ ከእሳቱ ፡ ወላፈን (፪x)
አዝ፦ በሠማይ ፡ በምድር ፡ ከቶ ፡ የለህ ፡ አቻ
ክበር ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ንገሥ ፡ አንተ ፡ ብቻ
መዝገቡም ፡ ይከፈት ፡ ታሪክም ፡ ይመርመር
አንደበትም ፡ ያውራ ፡ መስካሪም ፡ ይመስክር
ብርቱ ፡ የሆነ ፡ አምላክ ፡ ማነው ፡ ከአንተ ፡ በቀር
የሚነደውን ፡ እሳት ፡ በእሳት ፡ የሚሽር (፪x)
አዝ፦ በሠማይ ፡ በምድር ፡ ከቶ ፡ የለህ ፡ አቻ
ክበር ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ንገሥ ፡ አንተ ፡ ብቻ
|