ኃይልን ፡ የሚያስታጥቀኝ (Hailen Yemiyastateqegn) - አስቴር ፡ ዮሴፍ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስቴር ፡ ዮሴፍ
(Aster Yosef)

Aster Yosef 3.jpg


(3)

አንተው ፡ ትሻለኛለህ
(Antew Teshalegnaleh)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 6:58
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ ዮሴፍ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Yosef)

አዝ፦ ኃይልን ፡ የሚያስታጥቀኝ ፡ መንገዴን ፡ የሚያቀና
እግሮቼን ፡ እንደ ፡ ብሆር ፡ እግሮች ፡ የሚያበረታ
በኮረብቶች ፡ ላይ ፡ ሊያቆመኝ ፡ የወደደዉ
ለእጆቼ ፡ ሰልፍን ፡ ዘመቻን ፡ ያስተማረዉ
(፪x)
ብርቱ ፡ አድርጐ ፡ ያቆመኝ ፡ ብርቱ ፡ አድርጐ (፬x)

ይሄ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ ይሄ ፡ ነዉ
ይሄ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ እርሱ ፡ ይሄ ፡ ነዉ
ይሄ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ ይሄ ፡ ነዉ
ብርቱ ፡ አድርጐ ፡ የሚያቆም ፡ ብርቱ ፡ አድርጐ (፬x)

አስጨናቂዎቼ ፡ የለጠጡብኝ ፡ ቀስት ፡ ከቶ ፡ አልደረሰብኝ (፪x)
ብርቱ ፡ ተዋጊ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ እግዚአብሔር ፡ በዓይኑ ፡ ሰበረልኝ (፪x)
ከመቅደሱ ፡ ጢስ ፡ ወጥቶ ፡ ጠላቴን ፡ በተነ
የማይወድቅ ፡ የመሰለውን ፡ ብርቱውን ፡ ዘረረ
(፪x)

አዝ፦ ኃይልን ፡ የሚያስታጥቀኝ ፡ መንገዴን ፡ የሚያቀና
እግሮቼን ፡ እንደ ፡ ብሆር ፡ እግሮች ፡ የሚያበረታ
በኮረብቶች ፡ ላይ ፡ ሊያቆመኝ ፡ የወደደዉ
ለእጆቼ ፡ ሰልፍን ፡ ዘመቻን ፡ ያስተማረዉ
(፪x)
ብርቱ ፡ አድርጐ ፡ ያቆመኝ ፡ ብርቱ ፡ አድርጐ (፬x)

እጁ ፡ ተዘርግቷል ፡ ማንም ፡ አይመልስም (፫x)
እርሱን ፡ የሚነካ ፡ ማን ፡ አለ ፡ የሚደፍረው (፫x)
የየቀኖቹ ፡ ክፋት ፡ እኔን ፡ እንደሚያገኘኝ
በክንፎቹ ፡ ጋርዶ ፡ በቀኙ ፡ ሰወረኝ
(፪x)

አዝ፦ ኃይልን ፡ የሚያስታጥቀኝ ፡ መንገዴን ፡ የሚያቀና
እግሮቼን ፡ እንደ ፡ ብሆር ፡ እግሮች ፡ የሚያበረታ
በኮረብቶች ፡ ላይ ፡ ሊያቆመኝ ፡ የወደደዉ
ለእጆቼ ፡ ሰልፍን ፡ ዘመቻን ፡ ያስተማረዉ
(፪x)
ብርቱ ፡ አድርጐ ፡ ያቆመኝ ፡ ብርቱ ፡ አድርጐ (፬x)

ተስፋ ፡ ያደረግሁት ፡ አምላኬ ፡ ብርቱ ፡ ነው
ብርቱ ፡ አድርጐ ፡ አቆመኝ ፣ ብርቱ ፡ አድርጐ ፡ አቆመኝ
ለእጆቼ ፡ ሰልፍን ፡ ለጠላቴም ፡ ዘመቻን
ውጊያን ፡ አስተማረኝ ፣ ውጊያን ፡ አስተማረኝ
በጠላቴ ፡ ፊት ፡ ለፊት ፡ በዘይቱ ፡ ቀባኝ
ሙ ሉ ፡ ኃይልን ፡ አስታጥቆ ፡ በክብር ፡ አቆመኝ
(፪x)

አዝ፦ ኃይልን ፡ የሚያስታጥቀኝ ፡ መንገዴን ፡ የሚያቀና
እግሮቼን ፡ እንደ ፡ ብሆር ፡ እግሮች ፡ የሚያበረታ
በኮረብቶች ፡ ላይ ፡ ሊያቆመኝ ፡ የወደደዉ
ለእጆቼ ፡ ሰልፍን ፡ ዘመቻን ፡ ያስተማረዉ
(፪x)
ብርቱ ፡ አድርጐ ፡ ያቆመኝ ፡ ብርቱ ፡ አድርጐ (፬x)

ይሄ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ ይሄ ፡ ነዉ
ይሄ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ እርሱ ፡ ይሄ ፡ ነዉ
ይሄ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ ይሄ ፡ ነዉ
ብርቱ ፡ አድርጐ ፡ የሚያቆም ፡ ብርቱ ፡ አድርጐ (፬x)