From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
የትኛው ፡ ወዳጅ ፡ ነው ፡ የትኛው ፡ አባት
እስከ ፡ ዛሬ ፡ ድረስ ፡ ሳይደክም ፡ ሳይታክት
ሊሸከም ፡ የሚወድ ፡ ከኃጥያት ፡ ከነክፋቴ
ጌታ ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ አየሁ ፡ ፍፁም ፡ አፍቃሪዬ
ገረመኝ ፣ ገረመኝ ፣ ገረመኝ (፬x)
ይገርማል ፡ መወደዴ ፡ ይገርማል ፡ መፈለጌ
ይገርማል ፡ መመረጤ ፡ ይገርማል፡ መፈጠሬ
ገረመኝ ፣ ገረመኝ ፣ ገረመኝ (፬x)
ንጉሥ ፡ አዋጅ ፡ ቢያውጅ ፡ ጠላቴ ፡ ተጣድፎ
እርግማን ፡ ሊረግመኝ ፡ ባላቅም ፡ ተቻኩሎ
በለአም ፡ ግን ፡ ትእዛዝ ፡ ከላይ ፡ ተቀበለ
አዋጅ ፡ ሻረ ፡ ጌታ ፡ ታሪክ ፡ ተለወጠ
ገረመኝ ፣ ገረመኝ ፣ ገረመኝ (፪x)
ደነቀኝ ፣ ደነቀኝ ፣ ደነቀኝ (፪x)
ይገርማል ፡ መታሰቤ ፡ በዓይኖቹ ፡ መታየቴ
ገረመኝ ፡ እኔ ፡ መትረፌ ፡ በእጆቹ ፡ መያዜ
ገረመኝ ፣ ገረመኝ ፣ ገረመኝ (፫x)
የመኖሬን ፡ ሚስጢር ፡ ሳስብ ፡ ይደንቀኛል
ዛሬ ፡ ላይ ፡ መቆሜ ፡ እጅግ ፡ ይገርመኛል
አንተ ፡ ከላይ ፡ ሆነህ ፡ በዓይኖችህ ፡ አየኸኝ
ምህረት ፡ ማፅናናትህ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ አሰኘኝ
ገረመኝ ፣ ገረመኝ ፣ ገረመኝ (፪x)
ደነቀኝ ፣ ደነቀኝ ፣ ደነቀኝ (፪x)
ይገርማል ፡ መወደዴ ፡ ይገርማል ፡ መፈለጌ
ይገርማል ፡ መፈቀሬ ፡ ይገርማል ፡ መመረጤ
ገረመኝ ፣ ገረመኝ ፣ ገረመኝ
ደነቀኝ ፣ ደነቀኝ ፣ ደነቀኝ (፪x)
ማንም ፡ ያልራራልኝ ፡ መንገድ ፡ የተጣልኩኝ
በደም ፡ ተነክሬ ፡ ሞቴን ፡ የጠበቅሁኝ
በእጅህ ፡ ታክሜ ፡ ድኜ ፡ ከህመሜ
ከመሞት ፡ አምልጬ ፡ ገረመኝ ፡ መቆሜ
ገረመኝ ፣ ገረመኝ ፣ ገረመኝ (፬x)
ይገርማል ፡ ኧረ ፡ መትረፌ ፡ ከክፉዎች ፡ ማምለጤ
ገረመኝ ፡ አሰራርህ ፡ ፍጥነትህ ፡ አደራረስህ
ገረመኝ ፣ ገረመኝ ፣ ገረመኝ (፫x)
|