From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
የንጉሥ ፡ ልጅነት ፡ እንቢ ፡ ያለ
ግብፅንም ፡ በእምነት ፡ የተወ
ሳያየው ፡ እንደሚያየው ፡ ቆጥሮ
ብድራቱን ፡ አይቶ ፡ አሻግሮ
ምንም ፡ እንኳን ፡ የግብፅን ፡ ጥበብን ፡ ቢማርም
ሙሴ ፡ የባእድ ፡ ዕውቀት ፡ ከቶ ፡ አልማረከውም
ከገንዘብም ፡ ይልቅ ፡ መከራን ፡ መረጠ
ስለ ፡ ሥምህ ፡ ለአንተ ፡ መነቀፍን ፡ ወደደ
አዝ፦ ለጊዜያዊ ፡ እርካታና ፡ ደስታ
አለውጥም ፡ የነፍሴን ፡ ጌታ
ብድራቴን ፡ ልየው ፡ አሻግሬ
የዓለምን ፡ ዝናን ፡ ክብሯን ፡ ሁሉ ፡ ንቄ
አንተ ፡ ትሻለኛለህ (፰x)
አንተ ፡ ታዋጣኛለህ (፰x)
በቁጥቋጦው ፡ መሃል ፡ ታየኸው
እግዚአብሔር ፡ አምላኩ ፡ ቀረብከው
ሾምክና ፡ ወደ ፡ ሕዝብህ ፡ ላክኸው
በሞገስ ፡ ወጣህና ፡ አብረኸው
በብርታትህ ፡ ጉልበት ፡ የበረታ ፡ ሆነ
በድፍረት ፡ ንጉሥ ፡ ፊት ፡ ለመቆም ፡ ታመነ
የሰጠኸውን ፡ በትር ፡ በእምነት ፡ ይዞ ፡ ወጣ
እስራኤልን ፡ ከግብፅ ፡ ባርነት ፡ አወጣ
አዝ፦ ለጊዜያዊ ፡ እርካታና ፡ ደስታ
አለውጥም ፡ የነፍሴን ፡ ጌታ
ብድራቴን ፡ ልየው ፡ አሻግሬ
የዓለምን ፡ ዝናን ፡ ክብሯን ፡ ሁሉ ፡ ንቄ
አንተ ፡ ትሻለኛለህ (፰x)
አንተ ፡ ታዋጣኛለህ (፰x)
ትሁት ፡ ሆኖ ፡ ተመላለሰ
በህዝቡ ፡ መቃወም ፡ ታገሰ
እንዳለው ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ማለደ
ጥፋቱን ፡ ማየት ፡ መች ፡ ወደደ
ብድራቱን ፡ አይቶ ፡ ለዓላማው ፡ ጨክኖ
የንጉሥ ፡ ልጅ ፡ ሲባል ፡ በእምነት ፡ እንቢ ፡ ብሎ
ሳይፈራና ፡ ሳይደነግጥ ፡ የንጉሡን ፡ ቁጣ
በትሩን ፡ አነሳ ፡ ጠላትን ፡ ድል ፡ ነሳ
አዝ፦ ለጊዜያዊ ፡ እርካታና ፡ ደስታ
አለውጥም ፡ የነፍሴን ፡ ጌታ
ብድራቴን ፡ ልየው ፡ አሻግሬ
የዓለምን ፡ ዝናን ፡ ክብሯን ፡ ሁሉ ፡ ንቄ
አንተ ፡ ትሻለኛለህ (፰x)
አንተ ፡ ታዋጣኛለህ (፰x)
|