አምላኬ (Amlakie) - አስቴር ፡ ዮሴፍ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስቴር ፡ ዮሴፍ
(Aster Yosef)

Aster Yosef 3.jpg


(3)

አንተው ፡ ትሻለኛለህ
(Antew Teshalegnaleh)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 7:00
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ ዮሴፍ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Yosef)

አዝ፦ አምላኬ ፡ ከአማልክት ፡ በላይ
ታላቅ ፡ ነውና ፡ ሃሃ (፫x)
ጌታዬ ፡ ከአማልክት ፡ በላይ
ታላቅ ፡ ነውና ፡ ሃሃ (፫x)
በፊቱ ፡ እጣንን ፡ ከማጠን ፡ በቀር
አምልኮ ፡ ስግደትን ፡ ከማቅረብ ፡ በቀር
ምሥጋናን ፡ ዝማሬን ፡ ከመስጠት ፡ በቀር
ያለኝን ፡ በፊቱ ፡ ከማፍሰስ ፡ በቀር
ሌላ ፡ ምን ፡ እሰጥሃለሁ ፡ ሌላ (፬x)

ሠማይ ፡ ከሠማያት ፡ በላይ
ከፍ ፡ ብሎ ፡ ቢኖር ፡ ሌላ ፡ ሠማይ
ጌታዬን ፡ ሊይዘው ፡ አይችልም
ነውና ፡ ከሁሉም ፡ የበላይ (፪x)

የለውም ፡ የበላይ ፡ የበላይ ፡ የለውም ፡ የበላይ
እርሱ ፡ ነው ፡ የበላይ ፡ የበላይ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ የበላይ
ጌታዬ ፡ ነው ፡ የበላይ ፡ የበላይ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የበላይ

አዝ፦ አምላኬ ፡ ከአማልክት ፡ በላይ
ታላቅ ፡ ነውና ፡ ሃሃ (፫x)
ጌታዬ ፡ ከአማልክት ፡ በላይ
ታላቅ ፡ ነውና ፡ ሃሃ (፫x)
በፊቱ ፡ እጣንን ፡ ከማጠን ፡ በቀር
አምልኮ ፡ ስግደትን ፡ ከማቅረብ ፡ በቀር
ምሥጋናን ፡ ዝማሬን ፡ ከመስጠት ፡ በቀር
ያለኝን ፡ በፊቱ ፡ ከማፍሰስ ፡ በቀር
ሌላ ፡ ምን ፡ እሰጥሃለሁ ፡ ሌላ (፬x)

አየሁኝ ፡ የእርሱን ፡ ታላቅነት
ተረዳሁ ፡ የብርታቱን ፡ ጉልበት
ፅኑ ፡ ነው ፡ የለም ፡ ከእርሱ ፡ በቀር
በሠማይ ፡ ቢሆን ፡ በዚህች ፡ ምድር (፪x)

እርሱ ፡ ነው ፡ የበላይ ፡ የበላይ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ የበላይ (፪x)
ጌታዬ ፡ ነው ፡ የበላይ ፡ የበላይ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የበላይ

አዝ፦ አምላኬ ፡ ከአማልክት ፡ በላይ
ታላቅ ፡ ነውና ፡ ሃሃ (፫x)
ጌታዬ ፡ ከአማልክት ፡ በላይ
ታላቅ ፡ ነውና ፡ ሃሃ (፫x)
በፊቱ ፡ እጣንን ፡ ከማጠን ፡ በቀር
አምልኮ ፡ ስግደትን ፡ ከማቅረብ ፡ በቀር
ምሥጋናን ፡ ዝማሬን ፡ ከመስጠት ፡ በቀር
ያለኝን ፡ በፊቱ ፡ ከማፍሰስ ፡ በቀር
ሌላ ፡ ምን ፡ እሰጥሃለሁ ፡ ሌላ (፬x)

በብርቱ ፡ ጉልበቱ ፡ ታመንኩኝ
በፅድቅም ፡ ስራው ፡ ተመካሁኝ
በክንዱ ፡ ሁሉንም ፡ ያዘዘ
የምድርን ፡ ዳርቻ ፡ የያዘ
ላድንቀው ፡ ዛሬም ፡ የእኔን ፡ ጌታ
ላክብረው ፡ በጣፋጩ ፡ ዜማ
ገዥ ፡ ነህ ፡ ሁሉንም ፡ የረታህ
እያልኩኝ ፡ የለህም ፡ የበላይ

የለህም ፡ የበላይ ፡ የበላይ ፡ የለህም ፡ የበላይ (፪x)
አንተ ፡ ነህ ፡ የበላይ ፡ የበላይ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የበላይ (፪x)