አቤቱ ፡ በአንተ ፡ ታምኛለሁ (Abietu Beante Tamegnalehu) - አስቴር ፡ ዮሴፍ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስቴር ፡ ዮሴፍ
(Aster Yosef)

Aster Yosef 3.jpg


(3)

አንተው ፡ ትሻለኛለህ
(Antew Teshalegnaleh)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 7:55
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ ዮሴፍ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Yosef)

አቤቱ ፡ በአንተ ፡ ታምኛለሁኝ (፪x)
ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ታምኛለሁኝ (፪x)
አንተ ፡ አምላኬ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
አንተ ፡ ንጉሤ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
መታመኛዬ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም ፣ ለዘለዓለም
(፪x)

ከአንተ ፡ በቀር ፡ በጐነት ፡ የለኝም ፡ ጌታ
ከአንተ ፡ በቀር ፡ በጐነት ፡ የለኝም
ከአንተ ፡ በቀር ፡ በጐነት ፡ የለኝም ፡ ኢየሱስ
ከአንተ ፡ በቀር ፡ በጐነት ፡ የለኝም (፪x)

የተማመንኩብህ ፡ የነፍሴ ፡ አለኝታዬ
ለሕይወቴም ፡ ዋስትና ፡ ሆነሃል ፡ ጌታዬ (፪x)
መንፈሴን ፡ በሐሴት ፡ በደስታ ፡ ሞልተህ
ያለ ፡ አንዳች ፡ ሥጋት ፡ ታኖረኛለህ ፣ ታኖረኛለህ

ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ ፡ ጌታ
ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ
ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ
ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ (፪x)

የውስጥ ፡ የልቤን ፡ በር ፡ በፍቅር ፡ አንኳኩተህ
ክፈትልኝ ፡ ብለህ ፡ ፈቃዴን ፡ ጠይቀህ ፡ ወደ ፡ ልቤ ፡ ገብተህ
ድካምሽን ፡ ስጭኝ ፡ እኔ ፡ ልሸከመው
የሚል ፡ የልብ ፡ ወዳጅ ፡ ጌታ ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ አየሁ (፪x)

ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ ፡ ጌታ
ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ
ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ
ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ (፪x)

አቤቱ ፡ በአንተ ፡ ታምኛለሁኝ (፪x)
ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ታምኛለሁኝ (፪x)
አንተ ፡ አምላኬ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
አንተ ፡ ንጉሤ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
መታመኛዬ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም ፣ ለዘለዓለም
(፪x)

ከአንተ ፡ በቀር ፡ በጐነት ፡ የለኝም ፡ ጌታ
ከአንተ ፡ በቀር ፡ በጐነት ፡ የለኝም
ከአንተ ፡ በቀር ፡ በጐነት ፡ የለኝም ፡ ኢየሱስ
ከአንተ ፡ በቀር ፡ በጐነት ፡ የለኝም (፪x)

መሸከም ፡ ቢያቅተኝ ፡ የሸክሙን ፡ ክብደት
በፊትህ ፡ አስቀመጥኩት ፡ የጉድለቴን ፡ ብዛት (፪x)
እርዳታህ ፡ ከሠማይ ፡ ሲመጣልኝ ፡ ድንገት
የከበደኝ ፡ ሁሉ ፡ ተንሳፎ ፡ አየሁት (፪x)

ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ ፡ ጌታ
ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ
ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ
ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ (፪x)