ዛሬም ፡ ጉልበታም ፡ ነኝ (Zariem Gulbetam Negn) - አስቴር ፡ ሞገስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስቴር ፡ ሞገስ
(Aster Moges)

Lyrics.jpg


(1)

እኔ ፡ አልወርድም
(Enie Alwerdem)

ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ ሞገስ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Moges)

ዛሬም ፡ ጉልበታም ፡ ነኝ ፡ እንደ ፡ ትላንቱ
ጉልበቴ ፡ አልደከመም ፡ አድርጐኝ ፡ ብርቱ
መች ፡ ይሆንልኛል ፡ እኔስ ፡ ሳልይዘው
ያንን ፡ ተራራዉ
መች ፡ ይሆንልኛል ፡ እኔስ ፡ ሳልይዘው
ያንን ፡ ኮረብታዉ
ዛሬም ፡ ጉልበታም ፡ ነኝ ፡ እንደ ፡ ትላንቱ
ዛሬም ፡ ጉልበታም ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ አልደከምኩ

ምን ፡ ቁመቱ ፡ ቢረዝም ፡ ምን ፡ በፊቴ ፡ ቢገዝፍ
ምን ፡ ቁመቱ ፡ ቢረዝም ፡ ምን ፡ በፊቴ ፡ ቢገዝፍ
እኔን ፡ በፍፁም ፡ አያስፈራራኝ
ከእኔ ፡ ጋር ፡ ያለው ፡ ነው ፡ አስተማማኝ
(፪x)

አሃ ፡ አሃ ፡ እኔስ ፡ አልፈራ
አሃ ፡ አሃ ፡ አልደነግጥ (፪x)

እርሱ ፡ እየሄደ ፡ ከእኔ ፡ ፊት ፡ ፊት
እርሱ ፡ እየመራ ፡ ከእኔ ፡ ፊት ፡ ፊት
እርሱ ፡ እየወጣ ፡ ከእኔ ፡ ፊት ፡ ፊት
እየቀደመ ፡ ከእኔ ፡ ፊት ፡ ፊት
እኔስ ፡ አልፈራ ፡ አልደነትጥ (፪x)

ዛሬም ፡ ጉልበታም ፡ ነኝ ፡ እንደ ፡ ትላንቱ
ጉልበቴ ፡ አልደከመም ፡ አድርጐኝ ፡ ብርቱ
መች ፡ ይሆንልኛል ፡ እኔስ ፡ ሳልይዘው
ያንን ፡ ተራራዉ
መች ፡ ይሆንልኛል ፡ እኔስ ፡ ሳልይዘው
ያንን ፡ ኮረብታዉ
ዛሬም ፡ ጉልበታም ፡ ነኝ ፡ እንደ ፡ ትላንቱ
ዛሬም ፡ ጉልበታም ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ አልደከምኩ

ጥላቸው ፡ ወጥቶ ፡ እየገፈፈ
እግዚአብሔር ፡ ቀድሞ ፡ እያለፈ
በርስቴ ፡ ላይ ፡ የተመሰጉት
እግዚአብሔር ፡ በኃይሉ ፡ ሲበትን
ሁሉን ፡ በእጄ ፡ አሳልፎ ፡ ሰጥቶኛል
እድል ፡ ፈንታዬ ፡ ጌታ ፡ ሆኖልኛል
(፪x)

አሃ ፡ አሃ ፡ እኔስ ፡ አልፈራ
አሃ ፡ አሃ ፡ አልደነግጥ (፪x)

እርሱ ፡ እየሄደ ፡ ከእኔ ፡ ፊት ፡ ፊት
እርሱ ፡ እየመራ ፡ ከእኔ ፡ ፊት ፡ ፊት
እርሱ ፡ እየወጣ ፡ ከእኔ ፡ ፊት ፡ ፊት
እየቀደመ ፡ ከእኔ ፡ ፊት ፡ ፊት
እኔስ ፡ አልፈራ ፡ አልደነትጥ (፪x)

ጥላቸው ፡ ወጥቶ ፡ እየገፈፈ
እግዚአብሔር ፡ ቀድሞ ፡ እያለፈ
በርስቴ ፡ ላይ ፡ የተመሰጉት
እግዚአብሔር ፡ በኃይሉ ፡ ሲበትን
ሁሉን ፡ በእጄ ፡ አሳልፎ ፡ ሰጥቶኛል
እድል ፡ ፈንታዬ ፡ ጌታ ፡ ሆኖልኛል
(፬x)