ያመንኩትን ፡ አውቃለሁ (Yamenkuten Awqalehu) - አስቴር ፡ ሞገስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስቴር ፡ ሞገስ
(Aster Moges)

Lyrics.jpg


(1)

እኔ ፡ አልወርድም
(Enie Alwerdem)

ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ ሞገስ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Moges)

ያመንኩትን ፡ አውቃለሁ ፡ የተረዳሁትን
አንዱም ፡ አይጣል ፡ ከእርሱ ፡ የሰማሁት
በእጄ ፡ እንዳለ ፡ እንደጨበትኩት
ያህል ፡ ነው ፡ የምቆጥረው ፡ እንደያዝኩት (፪x)

አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ እርሱ ፡ ይታመናል
ከተናገረው ፡ የቱንስ ፡ አስቀርቷል
አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ እጅግ ፡ ይታመናል
ካለበት ፡ ቀን ፡ እልት ፡ መቼ ፡ ፈቀቅ ፡ ብሏል (፪x)

እለት ፡ እለት ፡ እርሱን ፡ ሳወጣና ፡ ሳወርደዉ
ቃሉን ፡ በአፌ ፡ አኑሬ ፡ እርሱን ፡ ብቻ ፡ ሳመላልሰዉ
ጥቅልሉን ፡ ስፈታ ፡ ውሉን ፡ ይዤ ፡ ስተረትረዉ
በዓይን ፡ ያልታየው ፡ ይገለጣል ፡ ጆሮ ፡ ያልሰማው (፪x)

ቃል ፡ ከአፉ ፡ ሲወጣ ፡ አልጠራጠረዉም
በልቤ ፡ አኑሬ ፡ እምጠባበቀዉም
ፈጽሞ ፡ አይሆንልኝ ፡ ችላ ፡ ችላ ፡ ማለት
እይዘለለ ፡ ውስጤ ፡ መች ፡ ይሰጠኝ ፡ እረፍት (፪x)

አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ እርሱ ፡ ይታመናል
ከተናገረው ፡ የቱንስ ፡ አስቀርቷል
አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ እጅግ ፡ ይታመናል
ካለበት ፡ ቀን ፡ እልት ፡ መቼ ፡ ፈቀቅ ፡ ብሏል (፪x)

ጌታዬ ፡ ብዬ ፡ አመልክሃለሁ
ወዳጄ ፡ ብዬ ፡ አመልክሃለሁ (፪x)