From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ረድኤቴ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ
ዛሬም ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ አለህ ፡ ጉዳይ
የጀመርከውን ፡ ሳትጨርሰዉ
አታርፍምና ፡ ሳትፈጽመዉ (፪x)
ልቤን ፡ አሰፋህ ፡ ውስጤን ፡ አሰፋህ
ዙሪያዬን ፡ አሰፋህ ፡ አንተ ፡ ስትመጣ (፪x)
እጀህ ፡ ተዘርግቷል ፡ ማን ፡ ሊመልሰው
በረከትን ፡ ከላይ ፡ ሊያዠቅዢቀው (፬x)
ብቻህን ፡ ክበር ፡ አንተው ፡ ንጉሥ
የጌቶቹ ፡ ጌታ ፡ በክብር ፡ ተመላለስ (፪x)
አንተ ፡ ማንንም ፡ ጌታ ፡ የማትረሳ
ሁሉም ፡ በጊዜው ፡ አንተ ፡ የምታነሳ
የተናገርከውን ፡ አታዘገየው
እጅ ፡ በእጅ ፡ ውዲያው ፡ ሳታወራርደው (፪x)
ፊትህ ፡ አበራ ፡ ሞገስህ ፡ አበራ
ክብርህ ፡ አበራ ፡ አንተን ፡ ስጣራ (፪x)
ድጆች ፡ ተከፈቱ ፡ ተነቀለ ፡ መዝጊያው
በቃ ፡ ተሰበረ ፡ የብረት ፡ መወርወሪያው (፬x)
ብቻህን ፡ ክበር ፡ አንተው ፡ ንጉሥ
የጌቶቹ ፡ ጌታ ፡ በኃይል/በክብር ፡ ተመላለስ (፪x)
ተመላለስ ፡ በኃይልህ
ተመላለስ ፡ በክብርህ (፬x)
|