ቀናቶቼ ፡ በከንቱ (Qenatochie Bekentu) - አስቴር ፡ ሞገስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስቴር ፡ ሞገስ
(Aster Moges)

Lyrics.jpg


(1)

እኔ ፡ አልወርድም
(Enie Alwerdem)

ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ ሞገስ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Moges)

ቀናቶቼ ፡ በከንቱ ፡ ዓመታቶቼ ፡ በችኮላ
እንዲሁ ፡ እንዳያልፉ ፡ ከዚህ ፡ በኋላ
ዘመኔን ፡ በሙሉ ፡ በፊቴ ፡ ያለውን
ያለ ፡ ፍሬ ፡ እንዳልሆን ፡ አስታጥቀኝ ፡ ኃይልን

አዝነፍሴ ፡ በኃይል ፡ በኃይል ፡ በኃይል ፡ እርግጥ ፡ ይሂ (፪x)
ወደላይ ፡ ወደላይ ፡ ወደላይ ፡ ውጪ (፪x)
ነፍሴ ፡ በኃይል ፡ በኃይል ፡ በኃይል ፡ እርግጥ ፡ ይሂ

እልፍ ፡ እልፍ ፡ እልፍ ፡ አያልኩኝ
የኋላዬን ፡ ወደኋላ ፡ እየተውኩኝ
የተያዝኩበትን ፡ ለመያዝ ፡ ፈጥናለሁ
ያለዋላ ፡ ማየት ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ እሻለሁ

አዝነፍሴ ፡ በኃይል ፡ በኃይል ፡ በኃይል ፡ እርግጥ ፡ ይሂ (፪x)
ወደላይ ፡ ወደላይ ፡ ወደላይ ፡ ውጪ (፪x)
ነፍሴ ፡ በኃይል ፡ በኃይል ፡ በኃይል ፡ እርግጥ ፡ ይሂ

ስለእኔ ፡ የሚያስበው ፡ ዘውትር ፡ መልካም ፡ ነው
በጅምር ፡ የማይቀር ፡ ፍጻሜ ፡ ያለው
የሚዳሰስ ፡ የሚጨበጥ ፡ አያለሁ ፡ ከዚህ ፡ የሚበልጥ (፪x)
(የሚጠነቀቅልኝ)
የሚዳሰስ ፡ የሚጨበጥ ፡ አያለሁ ፡ ከዚህ ፡ የሚበልጥ (፪x)

ላልመለስበት ፡ እኔን ፡ ያስመለጠ
ብርሃኑን ፡ ልኮ ፡ ከእጆቼ ፡ ያስጣለ
እንደ ፡ ዓይኑ ፡ ብሌን ፡ የሚጠነቀቅልኝ
የታቹን ፡ አስጥሎ ፡ የላዩን ፡ አስያዘ

አዝነፍሴ ፡ በኃይል ፡ በኃይል ፡ በኃይል ፡ እርግጥ ፡ ይሂ (፪x)
ወደላይ ፡ ወደላይ ፡ ወደላይ ፡ ውጪ (፪x)
ነፍሴ ፡ በኃይል ፡ በኃይል ፡ በኃይል ፡ እርግጥ ፡ ይሂ

የሚዳሰስ ፡ የሚጨበጥ ፡ አያለሁ ፡ ከዚህ ፡ የሚበልጥ (፪x)
(የሚጠነቀቅልኝ)
የሚዳሰስ ፡ የሚጨበጥ ፡ አያለሁ ፡ ከዚህ ፡ የሚበልጥ (፪x)