መተማመኛዬ (Metemamegnayie) - አስቴር ፡ ሞገስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስቴር ፡ ሞገስ
(Aster Moges)

Lyrics.jpg


(1)

እኔ ፡ አልወርድም
(Enie Alwerdem)

ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ ሞገስ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Moges)

መተማመኛዬ ፡ የተማመንኩበት
አያሳፍረኝ ፡ የተደገፍኩት
በፍፁም ፡ አልሰጋ ፡ ግራም ፡ አይገባኝ
ሊያደርግ ፡ ያለውን ፡ ከእኔ ፡ አይሰውረኝ (፪x)

የእኔ ፡ ጌታ ፡ የታመነዉ
ቃሉን ፡ በሥራ ፡ የገለጠዉ
የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ የታመነዉ
በስጦታው ፡ አይጸጽተዉ (፪x)

ታማኝነቱ ፡ አጥብቆ ፡ ያዘኝ
መቼም ፡ ከእጆቹ ፡ እኔን ፡ ላይለቀኝ
በእኔ ፡ መጨከን ፡ አይሆንለት
ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ የእሱስ ፡ አያልቅም

ልበለው ፡ እንጂ ፡ ተባረክ (፫x)
አትለወጥም ፡ ተባረክ (፫x)
አንተ ፡ ታማኝ ፡ ነህ ፡ ተባረክ (፫x)
ተባረክ ፡ ጌታ ፡ ተባረክ
ተባረክ ፡ ሁሌ/ዘለዓለም ፡ ተባረክ (፪x)

በጌታ ፡ ተማምኖ ፡ ከመንገድ ፡ የቀረ
ማን ፡ አንገቱን ፡ የደፋ ፡ ማን ፡ ያቀረቀረ
አታፍሪም ፡ እንዳለ ፡ መቼ ፡ ያሳፍራል
ከመቅደሱ ፡ ሆኖ ፡ ድሉን ፡ ያፈጥነዋል (፪x)

የእኔ ፡ ጌታ ፡ የታመነዉ
ቃሉን ፡ በሥራ ፡ የገለጠዉ
የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ የታመነዉ
በስጦታው ፡ አይጸጽተዉ (፪x)

ታማኝነቱ ፡ አጥብቆ ፡ ያዘኝ
መቼም ፡ ከእጆቹ ፡ እኔን ፡ ላይለቀኝ
በእኔ ፡ መጨከን ፡ አይሆንለት
ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ የእሱስ ፡ አያልቅም

ልበለው ፡ እንጂ ፡ ተባረክ (፫x)
አትለወጥም ፡ ተባረክ (፫x)
አንተ ፡ ታማኝ ፡ ነህ ፡ ተባረክ (፫x)

ተባረክ ፡ ጌታ ፡ ተባረክ
ተባረክ ፡ ሁሌ/ዘለዓለም ፡ ተባረክ (፭x)