ገና ፡ ከመጀመሪያው (Gena Kemejemeriyaw) - አስቴር ፡ ሞገስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስቴር ፡ ሞገስ
(Aster Moges)

Lyrics.jpg


(1)

እኔ ፡ አልወርድም
(Enie Alwerdem)

ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ ሞገስ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Moges)

ገና ፡ ከመጀመሪያው ፡ ከዚያን ፡ ቀን ፡ ጀምሮ
አሁንም ፡ ሊሰራኝ ፡ እጅግ ፡ አሳምሮ
ፈቀቅ ፡ አደረገኝ ፡ እኔን ፡ ወደ ፡ ማዶ
ከፊት ፡ ይልቅ ፡ ሊያሳየኝ ፡ ሊያበራልኝ ፡ ወዶ

አዝ፦ ሁሉ ፡ በሁሉ ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ነገር ፡ ያውቃል
አምላኬ ፡ ስለእኔ ፡ አጅግ ፡ ግድ ፡ ይለዋል
በፍፁም ፡ አይደክም ፡ አይታክት ፡ ስለእኔ
በአንዳች ፡ አንዳልጐድል ፡ አይለይ ፡ ከእኔ

ድካሜን ፡ አይወድም ፡ ክብሬን ፡ ይናፍቃል
ሁሉን ፡ ስለሰጠኝ ፡ ሊያየኝ ፡ ይፈልጋል
ካሰበልኝ ፡ በታች ፡ እንደኖር ፡ አይፈቅድም
እርሱን ፡ ደስ ፡ የሚለው ፡ ያይልኝን ፡ ስፈጸም ፡ ነው

አዝ፦ ሁሉ ፡ በሁሉ ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ነገር ፡ ያውቃል
አምላኬ ፡ ስለእኔ ፡ አጅግ ፡ ግድ ፡ ይለዋል
በፍፁም ፡ አይደክም ፡ አይታክት ፡ ስለእኔ
በአንዳች ፡ አንዳልጐድል ፡ አይለይ ፡ ከእኔ

እንደ ፡ ንጋት ፡ ብርሃን ፡ ክብሩ ፡ እይጨመረ
ከክብር ፡ ወደ ፡ ክብሩ ፡ እያሸጋገረ
በከፍታዎቹ ፡ ላይ ፡ እንድራመድ
ዘወትር ፡ ይመራኛል ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ እንድልለት

አዝ፦ ሁሉ ፡ በሁሉ ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ነገር ፡ ያውቃል
አምላኬ ፡ ስለእኔ ፡ አጅግ ፡ ግድ ፡ ይለዋል
በፍፁም ፡ አይደክም ፡ አይታክት ፡ ስለእኔ
በአንዳች ፡ አንዳልጐድል ፡ አይለይ ፡ ከእኔ

ጌታዬ ፡ ነዉ ፡ (ጌታዬ) ፡ አምላኬ ፡ ነዉ
ጌታዬ ፡ ነዉ ፡ (ጌታዬ) ፡ አምላኬ ፡ ነዉ ፡ (አምላኬ ፡ ነው)
ለእኔ ፡ የሚራራዉ ፡ እኔን ፡ የሚረዳዉ (፪x)
እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው

ለእኔ ፡ የሚራራዉ ፡ እኔን ፡ የሚረዳዉ (፪x)
እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው