እግዚአብሔር ፡ እንደ ፡ ጨካኝ (Egziabhier Ende Chekagn) - አስቴር ፡ ሞገስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስቴር ፡ ሞገስ
(Aster Moges)

Lyrics.jpg


(1)

እኔ ፡ አልወርድም
(Enie Alwerdem)

ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ ሞገስ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Moges)

እልፍ ፡ እያለ ፡ የሚሄድ ፡ የኋላውን ፡ ጥሎ
የጌታውን ፡ ፍለጋ ፡ ዱካውን ፡ ተከትሎ
አስቀድሞ ፡ ይወጣል ፡ ልቡን ፡ እያስደፈረ
አስተውሎ ፡ ያደርጋል ፡ ዘመን ፡ እየመረመረ
(፪x)

እግዚአብሔር ፡ እንደ ፡ ጨካኝ ፡ እንደ ፡ ኃያል
በጠላቶቼ ፡ ላይ ፡ ወረደ ፡ እያንዳንዱን ፡ ሊበቀል (፪x)

ጠጠር ፡ ይዞ ፡ የማይፈራ ፡ አሃሃ
የጠላቶቹ ፡ ዛቻና ፡ ፉከራ ፡ እህህ (፪x)

ከአምላኩ ፡ የተማረው ፡ የሰማ ፡ ነው ፡ ያሸነፈው (፬x)

ህዝቡን ፡ ያሸበረው ፡ እስኪ ፡ የቱ ፡ ነው ፡ ብሎ
ከሰልፉ ፡ መሃል ፡ ይወጣል ፡ በአምላኩ ፡ ተማምሎ
ዋነኛውን ፡ ሳይጥለው ፡ እርሱ ፡ አያፈገፍግም
ጭፍራውን ፡ ሳይበትነው ፡ ደግሞ ፡ አይመለስም
(፪x)

እግዚአብሔር ፡ እንደ ፡ ጨካኝ ፡ እንደ ፡ ኃያል
በጠላቶቼ ፡ ላይ ፡ ወረደ ፡ እያንዳንዱን ፡ ሊበቀል (፪x)

ጠጠር ፡ ይዞ ፡ የማይፈራ ፡ አሃሃ
የጠላቶቹ ፡ ዛቻና ፡ ፉከራ ፡ እህህ (፪x)

ከአምላኩ ፡ የተማረው ፡ የሰማ ፡ ነው ፡ ያሸነፈው (፬x)

ይሄስ ፡ የማነው ፡ ጀግና ፡ የማነው ፡ እርሱ
ይሄስ ፡ የማነው ፡ ጐበዝ ፡ የማነው ፡ እርሱ (፪x)

አሳየው ፡ እንጂ ፡ ቆርጠህ ፡ እራሱን
አሳየው ፡ እንጂ ፡ ቆርጠህ ፡ አንገቱን (፪x)