አመሰግናለሁ (Amesegenalehu) - አስቴር ፡ ሞገስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስቴር ፡ ሞገስ
(Aster Moges)

Lyrics.jpg


(1)

እኔ ፡ አልወርድም
(Enie Alwerdem)

ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ ሞገስ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Moges)

ሁልጊዜ ፡ እግዚአብሔርን ፡ አመሰግናለሁ
ዘወትር ፡ እርሱን ፡ ብቻ ፡ እባርካለሁ
መሸ ፡ ብዬ ፡ አልልም ፡ እስኪነጋም ፡ አልጠብቅም
ሌቱም ፡ እያቅላላ ፡ ቀን ፡ እንዲሆን ፡ አውቃለሁ
ደጋግሜ ፡ ሳመሰግን ፡ ሥሙን ፡ እየጠራሁ

ጌታ ፡ ነው ፡ አሃሃ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ኦሆሆ
ሁሌ ፡ ሲሰራ ፡ አሃሃ ፡ ትክክል ፡ ነው ፡ ኦሆሆ
አደራረጉ ፡ አሃሃ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ኦሆሆ
ተዓምራቱ ፡ ኦሆሆ ፡ ብዙ ፡ ነው

እስኪ ፡ ላመስግነው ፡ ቃላቴ ፡ ይሰማ
ልቤ ፡ ከአንደበቴ ፡ ጋር ፡ እየተስማማ
ሌላ ፡ ሌላው ፡ ይቅር ፡ ስለእርሱ ፡ ልናገር
እጆቼም ፡ ይነሱ ፡ ስለሥሙ ፡ ክብር

ይኼ ፡ ጌታ ፡ የሁሉ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ አኸኸ (፫x)
የበላይ ፡ የበላይ ፡ ሁሌም ፡ የበላይ ፡ ነው ፡ አኸኸ (፫x)
ይኼ ፡ ጌታ ፡ የሁሉ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ አኸኸ (፫x)
የበላይ ፡ የበላይ ፡ ሁሌም ፡ የበላይ ፡ ነው ፡ አኸኸ (፫x)

ታላልቁ ፡ ሥራው ፡ ድንቅ ፡ ተዓምራቱ
ትኩር ፡ ብዬ ፡ ሳየው ፡ የእርሱ ፡ በጐነቱ
አላስቀምጥ ፡ አለኝ ፡ እየቀሰቀሰኝ
አመሰግነዋለሁ ፡ ተራው ፡ ስለደረሰኝ

ይኼ ፡ ጌታ ፡ የሁሉ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ አኸኸ (፫x)
የበላይ ፡ የበላይ ፡ ሁሌም ፡ የበላይ ፡ ነው ፡ አኸኸ (፫x)
ይኼ ፡ ጌታ ፡ የሁሉ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ አኸኸ (፫x)
የበላይ ፡ የበላይ ፡ ሁሌም ፡ የበላይ ፡ ነው ፡ አኸኸ (፫x)

ሁልጊዜ ፡ እግዚአብሔርን ፡ አመሰግናለሁ
ዘወትር ፡ እርሱን ፡ ብቻ ፡ እባርካለሁ
መሸ ፡ ብዬ ፡ አልልም ፡ እስኪነጋም ፡ አልጠብቅም
ሌቱም ፡ እያቅላላ ፡ ቀን ፡ እንዲሆን ፡ አውቃለሁ
ደጋግሜ ፡ ሳመሰግን ፡ ሥሙን ፡ እየጠራሁ

ይኼ ፡ ጌታ ፡ የሁሉ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ አኸኸ (፫x)
የበላይ ፡ የበላይ ፡ ሁሌም ፡ የበላይ ፡ ነው ፡ አኸኸ (፫x)
ይኼ ፡ ጌታ ፡ የሁሉ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ አኸኸ (፫x)
የበላይ ፡ የበላይ ፡ ሁሌም ፡ የበላይ ፡ ነው ፡ አኸኸ (፫x)

ጌታ ፡ ነው ፡ አሃሃ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ኦሆሆ
ሁሌ ፡ ሲሰራ ፡ አሃሃ ፡ ትክክል ፡ ነው ፡ ኦሆሆ
አደራረጉ ፡ አሃሃ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ኦሆሆ
ተዓምራቱ ፡ ኦሆሆ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)