ይሆንልኛል (Yehonelegnal) - አስቴር ፡ አበበ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስቴር ፡ አበበ
(Aster Abebe)

Aster Abebe 1.jpg


(1)

ክብር ፡ የበቃህ ፡ ነህ
(Keber Yebeqah Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፱ (2017)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 6:27
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ አበበ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Abebe)

ይሆንልኛል ፡ ይሳካልኛል
ሥጋት ፡ ሰፈሬን ፡ ከራቀ ፡ ሰንበትበት ፡ ብሏል (፬x)

አልረሳውም ፡ ማንነቴን
በደም ፡ ዋጋ ፡ መገዛቴን
ንጉሥ ፡ ከላይ ፡ ሆኖ ፡ እንዳየኝ
ልጄ ፡ ምርጤ ፡ ርስቴ ፡ እንዳለኝ (፪x)

በምሰማው ፡ ሌላ ፡ ውሸት
አልጥለውም ፡ ይህን ፡ ዕውነት
ንጉሥ ፡ ልጁን ፡ የላከልኝ
የተወደድኩ ፡ ምርጥ ፡ ዘር ፡ ነኝ (፪x)

አይሆንም ፡ አይሰምርም ፡ ያለው ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ ነው?
ሁኔታ ፡ ነው? ነቅቻለሁ!
ቃሉን ፡ በንጉሥ ፡ ቃል ፡ ሽራለሁ
ተደርጐልኛል ፡ ተሳክቶልኛል ፡ ይህን ፡ አውቃለሁ

አይሆንም ፡ አይሰምርም ፡ ያለው ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ ነው?
ጠላቴ ፡ ነው? ነቅቻለሁ!
ቃሉን ፡ በንጉሥ ፡ ቃል ፡ ሽራለሁ
ይሆንልኛል ፡ ይሳካልኛል ፡ ይህን ፡ አውቃለሁ

ቁም ፡ ነገር ፡ አድርጐት ፡ የእኔን ፡ ጉዳይ
ክብሩን ፡ ሁሉ ፡ ትቶ ፡ ወርዷል ፡ ከላይ
አቅሜን ፡ አውቃለሁ ፡ በእርሱ ፡ ያለኝን
የሆንኩትን ፡ ሆኖ ፡ ያረገኝን (፪x)

ደዌ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ላይሰለጥን፡ እርግማን ፡ በቤቴ ፡ እንዳይገኝ
ዝቅታ ፡ ላይሆንብኝ ፡ በላዬ፡ መሸነፍ ፡ መረታት ፡ ላያገኘኝ
ከፍ ፡ ላለ ፡ ሕይወት ፡ በክርስቶስ ፡ ታጭቻለሁ ፡ ይህ ፡ ነው ፡ ዕጣ ፡ ፈንታዬ
የሆንኩትን ፡ ሁሉ ፡ ሆኖልኛል ፡ በድል ፡ ተፈጽሟል ፡ ጐዳናዬ

ያለቀ ፡ ነው ፡ ያኔ ፡ ድሮ
የእኔ ፡ ጉዳይ ፡ የእኔ ፡ ኑሮ
በቀራኒዮ ፡ ተራራ ፡ ላይ
ተፈጽሟል ፡ ብሎኛል ፡ የእኔ ፡ ጉዳይ (፪x)