From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አለህ ፡ በውስጤ ፡ ሰላምህ ፡ በዝቶልኛል
አለህ ፡ በላዬ ፡ ድል ፡ ማድረግ ፡ ሆኖልኛል
አለህ ፡ ከጎኔ ፡ ስትረዳኝ ፡ አየሁህ
አለህ ፡ በቤቴ ፡ ህይወቴን ፡ አጣፈጥህ (፪x)
አዝ፦ መንፈስ ፡ ቅዱሰ ፡ መጽናኛዬ
አቅሜ ፡ ነህ ፡ ጉልበት ፡ ሃይሌ
አማላጄ ፡ ነህ ፡ ደጀኔ
አቅም ሀይሌ ፡ ጓደኛዬ
አንድ ፡ የሆነ ፡ ጉዳይ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ እስክትጨርስ ፡ ድረስ
አይደለም ፡ ለጊዜ ፡ ወደ ፡ አብ ፡ እስከምትመለስ
ሁሌም ፡ ክእኔ ፡ ጋር ፡ ነህ ፡ ሆነሃል ፡ ወዳጄ
በውስጤ ፡ በላዬ ፡ ከጎኔ ፡ ከደጄ (፪x)
አዝ፦ መንፈስ ፡ ቅዱሰ ፡ መጽናኛዬ
አቅሜ ፡ ነህ ፡ ጉልበት ፡ ሃይሌ
አማላጄ ፡ ነህ ፡ ደጀኔ
መበርቻዬ ፡ ጓደኛዬ
እውርነት ፡ ቀርቶ ፡ ማየት ፡ ጀምሬያለሁ
የልቦናዬን ፡ አይኖች ፡ በአንተን ፡ አግኝቻለሁ
ድፍርሱን ፡ ህይወቴን ፡ በምክርህ ፡ አጥርተሃል
ያላንተ ፡ እንደማልኖር ፡ ልቤ ፡ ይህን ፡ አውቋል (፪x)
አዝ፦ መንፈስ ፡ ቅዱሰ ፡ መበርቻዬ
አቅሜ ፡ ነህ ፡ ጉልበት ፡ ሃይሌ
አማላጄ ፡ ነህ ፡ ደጀኔ
አቅሜ ፡ ኃይሌ ፡ ጓደኛዬ
መጽናኛዬ ፡ ጓደኛዬ
አለኝታዬ ፡ ጓደኛዬ
መበርቻዬ ፡ መጽናኛዬ
አለኝታዬ ፡ ጕደኛዬ
|