ከማይመቹ ፡ ሁኔታዎቼ (Kemayemechu Hunietawochie) - አስቴር ፡ አበበ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስቴር ፡ አበበ
(Aster Abebe)

Aster Abebe 1.jpg


(1)

ክብር ፡ የበቃህ ፡ ነህ
(Keber Yebeqah Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፱ (2017)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 4:42
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ አበበ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Abebe)

ከማይመቹ ፡ ሁኔታዎቼ
ካልተመለሱ ፡ ጥያቄዎቼ
አንተን ፡ መጠጋት ፡ ተማርኩ ፡ ትዕግስትን
ያልክልኝ ፡ ብቻ ፡ ይሁን ፡ ማለትን (፪x)

እምነቴን ፡ ሊጨምር ፡ ሊያጠነክረኝ
በእርሱ ፡ መጓደዴን ፡ ከፍ ፡ ሊያደርግልኝ
ይበልጡን ፡ እንዳውቀው ፡ እርሱ ፡ ማን ፡ እንደሆነ
ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነገር ፡ በህይወቴ ፡ ሆነ (፪x)

ለእራሴ ፡ ከማውቀው ፡ በላይ
እንደምታውቅልኝ ፡ አውቄያለሁ (፪x)

ፈጥነህ ፡ ብትመጣ ፡ ብትገኝ ፡ በቤቴ
መቼ ፡ ያልፍ ፡ ነበር ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ በህይወቴ
እንዲህ ፡ ያለውን ፡ ስንፍና ፡ ከአፌ ፡ አላወጣም
ሟቹን ፡ ለማስነሳት ፡ እጆችህን ፡ አያጥሩም
ድንጋዩን ፡ አንከባለህ ፡ ግንዛቱን ፡ ፈተህ
ዳግም ፡ ማመላለስ ፡ ፍቃድህ ፡ ከሆነ
ሰው ፡ ሁሉ ፡ አልቅሶ ፡ ሲያበቃ ፡ ከጀመርክ
ይሁንልኝ ፡ እላለሁ ፡ ሁሉ ፡ እንደፈቃድህ

አይሆንም ፡ ስል ፡ ሆነ
አይነጋም ፡ ስልህ ፡ ነጋ
አልዘልቅም ፡ ስል ፡ ዘለቅኩ
በብዙ ፡ ጀገንኩኝ ፡ በእርሱ ፡ ስለተያዝኩ (፪x)

የትላንት ፡ ምሽቴ ፡ ምስጋናን : ወለደ
የዘገየው ፡ መልሴ ፡ በውበት ፡ ተገለጠ
የሌሊት ፡ ለቅሶዬ ፡ ሳቅን ፡ አመጣልኝ
ባንተ ፡ ጊዜ ፡ ሲሆን ፡ ነገሬ ፡ አጌጠልኝ

አይሆንም ፡ ስል ፡ ሆነ
አይነጋም ፡ ስልህ ፡ ነጋ
አልዘልቅም ፡ ስል ፡ ዘለቅኩ
በብዙ ፡ ጀገንኩኝ ፡ በእርሱ ፡ ስለተያዝኩ (፪x)
በብዙ ፡ በረታሁ ፡ በእርሱ ፡ ስለተያዝኩ
በብዙ ፡ ጀገንኩኝ ፡ በእርሱ ፡ ስለተያዝኩ
በብዙ ፡ በረታሁ ፡ በእርሱ ፡ ስለተያዝኩ

ከማይመቹ ፡ ሁኔታዎቼ
ካልተመለሱ ፡ ጥያቄዎቼ
አንተን ፡ መጠጋት ፡ ተማርኩ ፡ ትዕግስትን
ያልክልኝ ፡ ብቻ ፡ ይሁን ፡ ማለትን