Aster Abebe/Keber Yebeqah Neh/Keber Yebeqah Neh

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ አስቴር አበበ ርዕስ ክብር የበቃህ ነህ አልበም ክብር የበቃህ ነህ

አዝ ቀድሞም ክብር የበቃህ ነህ ፡ሞልቶ የተረፈህ ተገብቶህ እንጂ ማን ሰጥቶህ ያውቃል ስለጎደለህ አንሶብህ ምሥጋናና ክብር አደባባይ ወጥተህ ማትለምን ኢየሱሴ ትልቅ ነህ ምትደነቅ (፪x)

ቀን አንድ ተብሎ ሳይጀመር አንተኮ ስትመለክ ነበር ወር አንድ ተብሎ ሳይቆጠር አንተኮ ስትመለክ ነበር ዓመት በዓመት ላይ ሳይደመር አንተኮ ስትመለክ ነበር በዘመናት ዘመን ሳይጨመር አንተኮ ስትመለክ ነበር

ሳይባል በመጀመሪያ ሳትፈጥር ሰማይና ምድርን አዕዋፋት ባየር ላይ ሳይበሩ ሳትመሰርት በፊት ተራሮችን ገና ሳታበጅ ሰውን በጅህ ሳይወጣ እስትንፋስ ከአፍህ ሁሉ ነገር ምንም ባዶ እያለ ምሥጋናህ ግን ሞልቶ የተረፈ

አዝ ቀድሞም ክብር የበቃህ ነህ ሞልቶ የተረፈህ ተገብቶህ እንጂ ማን ሰጥቶህ ያውቃል ስለጎደለህ አንሶብህ ምሥጋናና ክብር አደባባይ ወጥተህ ማትለምን ኢየሱሴ ትልቅ ነህ ምትደነቅ (፪x)

ቀን አንድ ተብሎ ሳይጀመር አንተኮ ስትመለክ ነበር ወር አንድ ተብሎ ሳይቆጠር አንተኮ ስትመለክ ነበር ዓመት በዓመት ላይ ሳይደመር አንተኮ ስትመለክ ነበር በዘመናት ዘመን ሳይጨመር አንተኮ ስትመለክ ነበር

ሳይባል በመጀመሪያ ሳትፈጥር ሰማይና ምድርን አዕዋፋት ባየር ላይ ሳይበሩ ሳትመሰርት በፊት ተራሮችን ገና ሳታበጅ ሰውን በጅህ ሳይወጣ እስትንፋስ ከአፍህ ሁሉ ነገር ምንም ባዶ እያለ ምሥጋናህ ግን ሞልቶ የተረፈ

ቀድሞም ክብር የበቃህ ነህ ሞልቶ የተረፈህ ተገብቶህ እንጂ ማን ሰጥቶህ ያውቃል ስለጎደለህ አንሶብህ ምሥጋናና ክብር አደባባይ ወጥተህ ማትለምን ኢየሱሴ ትልቅ ነህ ምትደነቅ