ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተመስገን (Gieta Hoy Temesgen) - አስቴር ፡ አበበ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስቴር ፡ አበበ
(Aster Abebe)

Aster Abebe 1.jpg


(1)

ክብር ፡ የበቃህ ፡ ነህ
(Keber Yebeqah Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፱ (2017)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 6:27
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ አበበ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Abebe)

ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን
አድናቆት ፡ ያንስሃል ፡ ቢጨመር ፡ ቢጨመር ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተመስገን
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን
ይሄ ፡ ሁሉ ፡ ያንስሃል ፡ ቢጨመር ፡ ቢጨመር ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተመስገን

ለመንፈስ ፡ ድኅነቴ ፡ ምስራች ፡ የሰበከ
የልቤን ፡ መሰበር ፡ በቃሉ ፡ እውነት ፡ የጠገነ
ምርኮኛ ፡ የነበርኩትን ፡ ነጻነቴን ፡ ያወጀልኝ
በብዙ ፡ ለቅሶ ፡ ፈንታ ፡ መጽናናትን ፡ የላከልኝ

እጨምራለሁ ፡ ባያክልህ ፡ ባይመጥንም ፡ ጥግህም ፡ ባይደርስም
እጨምራለሁ ፡ ባያክልህ ፡ ባይመጥንም ፡ ጥግህም ፡ ባይደርስም

ለፍቅሬ ፡ መግለጫ ፡ ላድርግ ፡ የቻልኩትን
ጥሜን ፡ ባይቆርጥልኝ ፡ ባያረካም ፡ ውስጤን
ትናንትም ፡ ብያለሁ ፡ ዛሬም ፡ እደግመዋለሁ
መተኪያ ፡ የለህም ፡ እኔ ፡ እወድሃለሁ

ተመስገን ፤ ተመስገን ፤ ተመስገን ፤ ተመስገን
ተመስገን ፤ ተመስገን ፤ ተመስገን ፤ ተመስገን
ሌላ ፡ የለኝም ፡ የሚጨመር ፡ ኢየሱሴ ፡ ተመስገን (፪x)

ብዙ ፡ አድርገህልኛል ፡ ከቁጥር ፡ ያለፈ ፡ ከቃላት ፡ ያለፈ ፡ ከንግግር ፡ ያለፈ
ብዙ ፡ አድርገህልኛል ፡ ከቁጥር ፡ ያለፈ ፡ ከቃላት ፡ ያለፈ ፡ ከንግግር ፡ ያለፈ

የሕይወቴ ፡ ትርጉም ፡ ነህ ፡ የከፍታዬ ፡ ምክንያት
መዳን ፡ የሆንክላት ፡ ላንዷ ፡ ነፍሴ ፡ ወደህ ፡ የተቤዠሃት
ተስፋ ፡ የማደርግህ ፡ ትመጣለህ ፡ ብዬ
የእውነቱን ፡ ልናገር ፡ ከውስጥ ፡ ከመንፈሴ
ኑሮ ፡ መቃብር ፡ ነው ፡ ያላንተ ፡ ኢየሱሴ
የእውነቱን ፡ ልናገር ፡ ከውስጥ ፡ ከመንፈሴ
ኑሮ ፡ አይጥመኝም ፡ ያላንተ ፡ ኢየሱሴ