Aster Abebe/Keber Yebeqah Neh/Felegieh
ፈልጌህ ፡ አላጣሁህም ከልቤ ፡ ሽቼህ ፡ ራስህን ፡ አልሰወርክም (፪x)
ውሃ ፡ በሌለበት ፡ በደረቅ ፡ ምድር
ነፍሴ ፡ ተጠምታ ፡ አገኘችህ ፡ አገኘችህ አገኘችህ (2x
በቅቤና ፡ በስብ ፡ እንደሚረካ ፡ ሰው
ሳገኝህ ፡ ልቤን ፡ ደስ ፡ አለው (፪x)
ተመችቶኝ ፡ ነው ፡ አባትነትህ
ዘላለም ፡ በቤቴ ፡ እራስ ፡ ሁን ፡ የምልህ
ተመችቶኝ ፡ ነው ፡ አምላክነትህ
ዘላለም ፡ በላዬ ፡ ንገስብኝ ፡ ምልህ
አዛኝ ፡ ባትሆን ፡ ፍቅር ፡ ባትሆን ፡ አምላኬ ፡ ባትሆን ፡ ጌታዬ ፡ ባትሆን
ባትሸከመኝ ፡ በፍቅር ፡ ባትይዘኝ ፡ ፈቅደህ ፡ ባትምረኝ ፡ መክረህ ፡ ባትመልሰኝ
በፍቅር ፡ ባትይዘኝ ፡ ፈቅደህ ፡ ባትምረኝ ፡ ምክርህ ፡ ባይደግፈኝ
ምን ፡ ይሆን ፡ ነበረ ፡ ዕጣዬ
ስለምሕረትህ ፡ ተመስገን ፡ ጌታዬ (፪x)
አቅም ፡ የሆንክልኝ ፡ ተባረክ
ዘውዴ ፡ መድመቂያዬ ፡ ተባረክ
ቅድስናዬ ፡ ነህ ፡ ተባረክ
አብ ፡ ፊት ፡ መታያዬ ፡ ተባረክ (፪x)
ተባረክ ፡ ተባረክ ፤ ተባረክ ፡ ተባረክ
ተባረክ ፡ ተባረክ ፤ ተባረክ ፡ ተባረክ
እኔ ፡ ምፈልገው ፡ (አንተን ፡ ነው) (፫x) ሌላው ፡ በሙሉ (ቀሪ ፡ ነው) (፫x)
ሁሌ ፡ ምናፍቀው (አንተን ፡ ነው) (፫x) ሌላው ፡ በሙሉ (ቀሪ ፡ ነው) (፫x)
እኔ ፡ ምፈልገው ፡ አንተን ፡ ነው
ሌላው ፡ በሙሉ ፡ ቀሪ ፡ ነው
እኔ ፡ ምፈልገው ፡ አንተን ፡ ነው
ሌላው ፡ በሙሉ ፡ (ቀሪ ፡ ነው) (፮x)