Aster Abebe/Keber Yebeqah Neh/Esti Yengeregn

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

Aster Abebe ዘማሪ አስቴር አበበ ርዕስ እስቲ ይንገረኝ አልበም ክብር የበቃህ ነህ

እስኪ ይንገረኝ ሚያውቅ ካለ ስለእርሱ ጅማሬ እስኪ ይንገረኝ ሚያውቅ ካለ ስለእርሱ ፍጻሜ እስኪ ይንገረኝ ሚያውቅ ካለ ስለአካሄዱ እስኪ ይንገረኝ ሚያውቅ ካለ የአምላኬ መንገዱን (፪x)

ምን ማወራው አለኝ ካነበብኩት በቀር ከፍቅሩ በቀር ከምክሩ/ከነገሩኝ/ በቀር እንዴት እንደወጣሁ ያንን ክፉ ሰፈር /መንደር/ የማውቀው ይሄን ነው ስለጌታ ነገር (፪x)

የተማረ ሰው ብዙ የተተወለት መተላለፉ ኃጢአቱ የተረሳችለት አንተን ቢያመሰግንህ ቢልስ ጐንበስ ቀና አሳነሰብህ እንጂ መቼ ይበዛና (፪x)

የበዛውን የአንተን ምሕረት አይቼ የተትረፈረፈውን ፀጋህን ቀምሼ አንተን አለማምለክ ነውር ሆኖ ታየኝ ይልቅስ መጨመር መቀኘትን አሰኘኝ

ላመስግንህ (አሃ) ከፍ ላድርግህ (አሃ) ልቀኝልህ (አሃ) ልዘምርልህ የርህራሄ አምላክ ነህ ዓይኖቼ አይተውሃል ከትላንቱ ይልቅ ልቀርብህ ገዶኛል (፪x)

ምን ማወራው አለኝ ካነበብኩት በቀር ከፍቅሩ በቀር ከምክሩ/ከነገሩኝ/ በቀር እንዴት እንደወጣሁ ያንን ክፉ ሰፈር /መንደር/ የማውቀው ይሄን ነው ስለጌታ ነገር (፪x)