Aster Abebe/Keber Yebeqah Neh/Enkwanem Agegnehegn
ዘማሪ አስቴር አበበ ርዕስ እንኳንም አገኘኸኝ አልበም ክብር የበቃህ ነህ
የራቀ ሰፈሬን ጠንክሮ የታጠረ አጥሬን
ምክንያት ፈልጎ ፈጥሮ የራሱን ሰበብ
ተቀምጦ ቆየኝ ከጉድጓዱ አጠገብ (፪x)
ሳላውቀው ማንነቱን የነፍሴን መድሃኒት
እንዲህ እንዲያ እያልኩኝ ስደረድር ምክንያት
ለጥቆ ገባና ወደ ህይወቴ ባህር
ለራሴው ነገረኝ የእራሴን ሚስጥር
የሚጠጣ ውሃ በእኔ ዘንድ ፍለጋ
መች ቆመ ከደጄ እራሱን ሊያረካ
ህይወትን ሊችረኝ ከከበቡኝ ሁሉ
አፋቶ የእራሱ አደረገኝ በፍቅሩ
መስሎኝ በምድሩ ሰላምና እርካታ
ከአንዱ ተጋብቼ አንደኛውን ስፈታ
አይቶ መባከኔን በእርግጥ አዝኖልኛል
በአፉ ቃል እፎይታ ወደ ቤቴ ገብቷል
እንኳንም አገኘኸኝ አንተ ወዳጄ
እንኳንም ቀድመኸኝ ተገኘህ ከደጄ
ቢሆንማ ሌላው
ዛሬን በአይኔ ባላየሁ
ቤተ መድ ይስማ ጓደኛ ጎረቤት
ላፍታም አልዘገይም ሳልነግር ይህን እውነት ጉዴን ለነገረኝ የኋላ ታሪኬን
ልቤ እርሱ ጋር ቀርቷል ወስዶልኝ ሸክሜን
እንኳንም አገኘኸኝ አንተ ወዳጄ
እንኳንም ቀድመኸኝ ተገኘህ ከደጄ
ቢሆንማ ሌላው
ዛሬን በአይኔ ባላየሁ