በረኝነቱ (Beregnenetu) - አስቴር ፡ አበበ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስቴር ፡ አበበ
(Aster Abebe)

Aster Abebe 1.jpg


(1)

ክበር ፡ የበቃህ ፡ ነህ
(Keber Yebeqah Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፱ (2017)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 3:57
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ አበበ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Abebe)

በእረኝነቱ ፡ ተመርቻለሁ
ጠንቀቅ ፡ አድርጌም ፡ ድምፁን ፡ አውቃለሁ
በአረንጓዴው ፡ መስክ ፡ ባማረው ፡ ላይ
አንሰራፍቶኛል ፡ ሳይኖር ፡ ከልካይ

አልፈራም ፡ አውሬ ፡ ደፋር ፡ አርጎኛል
የአራዊት ፡ ድምፅ ፡ መቼ ፡ ያስፈራኛል
ባለመናወጥ ፡ ከምንጩ ፡ ልርካ
ከጭንቀት ፡ ማረፍ ፡ እንዲህ ፡ ነው ፡ ለካ

እንዲህ ፡ ነው ፡ ለካ ፡ አሃ
እንዲህ ፡ ነው ፡ ለካ (፬x)

ኧረ ፡ እንዴት ፡ ተለዪው ፡ ይሉኛል
ይህን ፡ የቅርብ ፡ ወዳጄን
ኧረ ፡ እንዴት ፡ ተለዪው ፡ ይሉኛል
ይህን ፡ የበረሃ ፡ ጓዴን
ኧረ ፡ እንዴት ፡ ተለዪው ፡ ይሉኛል
ይህን ፡ ሚስጢረኛዬን
ኧረ ፡ እንዴት ፡ ተለዪው ፡ ይሉኛል
ይህን ፡ መልካም ፡ እረኛዬን

አልለየውም ፡ አልለየውም
ያለ ፡ እርሱ ፡ መኖር ፡ እኔስ ፡ አልችልም
አልለየውም ፡ አልለየውም
ያለ ፡ እርሱ ፡ ውበት ፡ ወዝም ፡ የለኝም (፪x)

ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ያልኩትን ፡ ያለ ፡ ከፍታዬ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያረገኝ
ወገን ፡ ያልሆንኩትን ፡ በልጁ ፡ ልጅ ፡ አርጎ ፡ ማዕረግን ፡ ያሳየኝ
የተደረገውን ፡ በጎነት ፡ ቸርነት ፡ አልችልም ፡ መሸከም
የምልህ ፡ የለኝም ፡ በሰጠኸኝ ፡ ዘመን ፡ ከፊት ፡ ፊቴ ፡ ቅደም

ብርታቴ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ብርታቴ
ህይወቴ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ህይወቴ
ጉልበቴ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ጉልበቴ
ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ መድኃኒቴ (፪x)
መድኃኒቴ ፡ መድኃኒቴ (፪x)