ወደ ተራራው ጫፍ (Wede Teraraw Chaf) - አስቴር ፡ አበበ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አስቴር ፡ አበበ
(Aster Abebe)

Aster Abebe 2.png


(2)

ሃሌሉያ
(Hallelujah)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ አበበ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Abebe)

ከህልውናህ ፡ ሰፈር ፡ ከምትገኝበት
ንግግር ፡ ፀሎቴ ፡ አንተው ፡ ከሆንክበት
ጠንቀቅ ፡ ካላልኩኝ ፡ ካልጠበቅሁ ፡ እግሮቼን
እልፍ ፡ የሚለይ ፡ ጉዳይ ፡ ከቦኛል ፡ ዙሪያዬን

በገለባ ፡ ናፍቆት ፡ በጠፊ ፡ ፍለጋ
አይለፍብኝ ፡ ቀኔ ፡ አርቆኝ ፡ ካንተ ፡ ጋር
ወደተራራው ፡ ጫፍ ፡ ሳበኝ ፡ ወደራስህ
ነፍሴም ፡ ድና ፡ እንድትቀር ፡ አቅልጣት ፡ በክብርህ (፪x)

መባዘን ፡ አይደለም ፡ መዋል ፡ ካንተ ፡ ጋራ
ስለ ፡ ላዩ ፡ ምክርህ ፡ ነፍሴን ፡ ስታዋራ
ሰብሰብ ፡ ብሏል ፡ ቀኔ ፡ አልተዝረከረከም
የማይወሰድ ፡ እድል ፡ ከዚህ ፡ በላይ ፡ የለም

አንተን ፡ ብቻ ፡ ይሁን ፡ የማይበት ፡ ዓይኔ
ልቤም ፡ ሄዶ ፡ ይቅር ፡ ከላዩ ፡ ሰፈሬ
ጆሮዬም ፡ ይቀስር ፡ ከላይኛው ፡ ሃገር
አጥፋኝ ፡ ከምድሩ ፡ ፍለጋዬ ፡ ይሰወር

አንገቴን ፡ አስግጌ ፡ በመናፈቅ ፡ ህይወት
ለአፍታ ፡ ጎንበስ ፡ ሳልል ፡ አንዳች ፡ ከሌለበት
እጅ ፡ ሰጥቶ ፡ ላንተ ፡ ውስጥና ፡ ውጪዬ
ስንቄ ፡ ሆኖ ፡ ፍቅርህ ፡ ይጠቅለል ፡ እድሜዬ (፪x)

ጥሜ ፡ ረሃቤ ፡ ናፍቆቴ ፡ መሻቴ
ጉጉቴ ፡ ፍላጎቴ ፡ ሩጫዬ ፡ መገስገሴ
አንተን ፡ ለማግኘት ፡ ነው (፪x)

በቃ ፡ ፈልግሃለሁ ፡ በቃ ፡ ተርቤሃለሁ
በቃ ፡ በጣም ፡ ጠምተኸኛል ፡ በቃ ፡ አይኖቼ ፡ ናፍቀውሃል
በቃ ፡ ናፍቄሃለሁ ፡ በቃ ፡ ደጅ ፡ ደጅ ፡ አያለሁ
በቃ ፡ የውስጤ ፡ ጥም ፡ ነህ
በምንም ፡ የማልለውጥህ

አንተን ፡ የተራበ ፡ ሚጠግበው ፡ አንተን ፡ ነው
አንተን ፡ የተጠማ ፡ ሚረካው ፡ አንተን ፡ ነው
ፊትህን ፡ የፈለገ ፡ ሲያገኝህ ፡ ያርፋል
ፈልጎ ፡ ክብርህን ፡ መቼ ፡ በጅህ ፡ ይረካል

አይደለሁም ፡ ሰነፍ ፡ ተመከርኩ ፡ በቃልህ
የውስጤን ፡ እረሃብ ፡ አይደፍነውም ፡ የእጅህ
ነፍሴን ፡ የምታረካ ፡ ሙላት ፡ ነህ ፡ የልቤ
የኑሮዬ ፡ ፍሰሃ ፡ የዕድሜ ፡ ልክ ፡ ሃሳቤ