ስምህን ጠራሁ (Simihin Terahu) - አስቴር ፡ አበበ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አስቴር ፡ አበበ
(Aster Abebe)

Aster Abebe 2.png


(2)

ሃሌሉያ
(Hallelujah)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

፲ ፰ (18)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ አበበ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Abebe)

የማልተወው ቅኔ የማልተወው ቦታ
ማልረሳው ልማዴ የህይወቴ ተርታ
ካንተ ጋር መሆን ነው መክረም ባለህበት
የህይወቴ ዋና የእስትንፋሴ ርዝመት
ካንተ ጋር መሆን ነው መክረም ባለህበት
የህይወቴ ዋና የእስትንፋሴ ርዝመት

ካልደገፍከኝ ማልቆም ካልያዝከኝ የምወድቅ
ካልመራኸኝ የምስት ካላንተ የማልደምቅ
ሳትፈቅድልኝ የማልኖር የሆንክ እስትንፋሴ
ሁሉዬ ነህ እየሱሴ
ሳትፈቅድልኝ የማልኖር የሆንክ እስትንፋሴ
ሁሉዬ ነህ እየሱሴ

የሁሌ መናዬ ከላይ የወረድህ
በደረቅ መሬት ላይ ነፍሴን ያረጠብህ
ከሙታኖች ሰፈር ትንፋሽ ከሌለበት
ሆንክልኝ ድልድዬ አብን ምደርስበት
ሆንክልኝ ገመዴ አብን ምደርስበት

ስምህን ጠራሁ ደስ አለኝ
ቃልህን በላው ደስ አለኝ
መንፈስህ አጽናናኝ ቀለለኝ
አብሬህ ዋልኩኝ ደስ አለኝ

አንተን አግኝቼ ሌላ መሄጃ አላስፈለገኝ
አንተን ሰምቼ ሌላ የሚወራም አላስፈለገኝ
ባንተ ተጽናናው ሌላ ሲጨመር አላስደሰተኝ
ካንተጋ ቀየው ሌላ የሚያጽናና አላስፈለገኝ

ብቻህን በቃኸኝ/8