From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
አስቴር ፡ አበበ (Aster Abebe)
|
|
፪ (2)
|
ሃሌሉያ (Hallelujah)
|
ዓ.ም. (Year):
|
2024
|
ቁጥር (Track):
|
፲ ፫ (13)
|
ርዝመት (Len.):
|
9:14
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የአስቴር ፡ አበበ ፡ አልበሞች (Albums by Aster Abebe)
|
|
1.በፊትህ እስክጥለው የኔ ነበረ በትሩ
ፈቃዴን ማድረጊያ ያልታየኝ አቅሙ
ከምርኩዝ የማያልፍ የማይዘልቅ ከማገጃ
በእጄ የከረመ ድጋፍ መወጣጫ
ያን እለት ገብቶኛል ትኩረቴን ስትስበው
በሚነድ ቁጥቋጦ እግሬን ስታፈጥነው
የሰጠኝን መልሼ ብጥል ከእግሮችህ ስር
እንደ ምትሰራበት ባንተ እጅ
እንዲያምር አውቂያለሁኝ [ 2× ]
እንካ ጊዜዬን ተጠቀምበት
በልብህ እንዳለው አከናውንበት
እንካ ያለኝን ወርቅ እና ብር
እኔ ጋር ሆኖ ጓዳ እንዳይቀር [ 2× ]
2.ሁለት አሳና አምስት እንጀራ
ከኔ አያልፍም በሰው ሲሰላ
ለራሴ ነበር ሰንቄ የያዝኩት
ረሀቡ ሲጠና ብጎርሰው ያልኩት
የአንተ ግምት ከእኔ ካለፈ
ብዙ ልታጠግብ ከእጄ ወስደህ
እንቢ አልልም ስስት ለቆኛል
ከእኔ ቢወጣ እልፍን ይሸኛል [ 2× ]
አስደምሞኛል ተደንቂያለሁ
ጥቂት ነበረ በእጄ ላይ ሳየው
ይለፍ ካንቺ ካልክ አገር ሊያበላ
ይውጣልኝ ከእጄ ይሁን ለሌላ [ 2× ]
ይለፍ ካንተ ካልክ አገር ሊያበላ
ይውጣልኝ ከእጄ ይሁን ለሌላ [ 2× ]
3.ምን ክፋት አለው ቢያገለግለኝ
አገር ሁሉ ያውቃል እንደሰጠኸኝ
እንደተቀበልኩት በለቅሶ በእንባ
በስለት ክምር ቤቴ እንደገባ
ከሚሆን የራሴ እኔው ጋር ቀርቶ
መልሼ ልስጥህ ልይ ሌላውን በቅቶ
ስስት ሳይዘኝ እንዴ ሳልልህ
ይኸው አኖርኩት ከእግሮችህ ስር [ 2× ]
አሜን ይሁና ሳሙኤልን እንካ
ትርፍም ባይኖረኝ እሱን ሚተካ
አይቆይ ካንቺ ጋር ካልክ አምጪው ለኔ
ለትውልድ ይሁን ይለፈኝ እኔን [ 2× ]
አይቆይ ካንተ ጋር ካልክ አምጣው ለኔ
መልሼ ልስጥህ ይለፈኝ እኔን [ 2× ]
ሽታውን ሳልጠግበው የልጅነቱን 👩🍼
ነግቶልኝ ሳላይ ጨዋታ ሳቁን
ጥቂት ቆይቶ ሳያባብለኝ
እንካ በማለዳ ተቀበለኝ [ 2× ]
አሜን ይሁና ሳሙኤልን እንካ
ትርፍም ባይኖረኝ እሱን ሚተካ
አይቆይ ካንቺ ጋር ካልክ አምጪው ለኔ
ለትውልድ ይሁን ይለፈኝ እኔን [ 2× ]
አይቆይ ካንተ ጋር ካልክ አምጣው ለኔ
መልሼ ልስጥህ ይለፈኝ እኔን [ 2× ]
|