From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
የኔ ጌታ የኔ ውበት
የኔ ፍቅር የኔ ናፍቆት
የኔ ወዳጅ የኔ ውበት
የኔ ፍቅር የኔ ናፍቆት
መኖር አልችልም ያላንተ (2) እፈራለሁ
ሁሉም ክድንድን ያለ ነው
መኖር አልችልም ያላንተ (2) እፈራለሁ
ሁሉም ጭልምልም ያለ ነው
አሁንም እላለሁ ጥማኝ አሁንም እላለሁ ራበኝ
አሁንም እላለሁ ናፍቀኝ
አሁንም እላለሁ ጥማኝ አሁንም እላለሁ ራበኝ
አሁንም እላለሁ ናፍቀኝ በማንነትህ ልክ
የረሃቤ ቁመቱ ይላቅ ከከበበኝ
አይስረቅ እይታዬን ዘልቆ ላያዘልቀኝ
ከጎደለኝ ነገር ከምለው ይህ ቀረ
ይሁንልኝ ረሃቤ ለአንተ ያጋደለ
አሁንም እላለሁ ጥማኝ አሁንም እላለሁ ራበኝ
አሁንም እላለሁ ናፍቀኝ
አሁንም እላለሁ ጥማኝ አሁንም እላለሁ ራበኝ
አሁንም እላለሁ ናፍቀኝ በማንነትህ ልክ
አንተን ማጣት ነው ብቸኝነት
መጸለይ ማቆም ነው ድርቀት
መንፈስህን መተው ነው ክስረት
ውሎ ማደር አንተ በሌለህበት
ቃልህን መርሳት ነው ጎዶሎነት
ሳይሰሙህ መውጣት ነው ዙረት
ያለ ድምጽህ ማውራት ነው ቅዠት
ውሎ ማደር አንተ በሌለህበት
መኖር አልችልም ያላንተ (2) እፈራለሁ
ሁሉም ክድንድን ያለ ነው
መኖር አልችልም ያላንተ (2) እፈራለሁ
ሁሉም ጭልምልም ያለ ነው
አንተን ተከትዬ ቤቴ ወና ይቅር
ከአፈር የሆነው ይቅርብኝ በጅምር
በአንተ ብቻ ልመር ላጊጥ በሃሳብህ
ይልቀቀኝ የምድሩ ሳበኝ በፈቃድህ
አሁንም እላለሁ ጥማኝ አሁንም እላለሁ ራበኝ
አሁንም እላለሁ ናፍቀኝ
አሁንም እላለሁ ጥማኝ አሁንም እላለሁ ራበኝ
አሁንም እላለሁ ናፍቀኝ በማንነትህ ልክ
በተጨመረልኝ ዕድሜ በተቀጠሉልኝ ቀናት
ነፍሴን ዝም ጸጥ አሰኝቼ ከጌታ ውጭ ላልሰጣት
ነጥቄአት ከሌላው ጎዳና ትዋል ኮቴህ በሚረግጥበት
ልቤን እንዲህ አስፋልኝ እና ላጊጥ በፈቃድህ ውበት
ልመረቅ በእጆችህ ለማዶው ሽልማት
ፍለጋህ እንድከተል ጸጋህን ስጠኝ በብዛት
ትሁን ነፍሴ እንዳልካት ደስታህ ሃይሌ ነው
የሰማዩን ፈቃድህን በምድር ስኖረው
አሁንም እላለሁ ጥማኝ አሁንም እላለሁ ራበኝ
አሁንም እላለሁ ናፍቀኝ
አሁንም እላለሁ ጥማኝ አሁንም እላለሁ ራበኝ
አሁንም እላለሁ ናፍቀኝ በማንነትህ ልክ
|