ጉዳዬ (Gudaye) - አስቴር ፡ አበበ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አስቴር ፡ አበበ
(Aster Abebe)

Lyrics.jpg


(2)

Hallelujah
(Hallelujah)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

(2)

ጸሐፊ (Writer): አስቴር ፡ አበበ
(Aster Abebe
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ አበበ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Abebe)

ለሚያወራህ ውበት ለሚለብስህ ጌጥ
ሮጦ ለተጠጋህ የማምለጫ አለት
ህይወት ከሞት ወዲያ እርስቱ ላረገህ
ለአፍታ እንኩዋን የሚትጎድል ለሰው ሙላቱ ነህ
አንተን ነው እንጂ ጥብቅ አድርጎ መያዝ ያዘኝ እያሉ
ማልዶ በጠዋት በአንተው እጅ ደምቆ መዋል ደጅ እየጠኑ
አንተን ነው እንጂ ጥብቅ አድርጎ መያዝ ያዘኝ እያሉ
ማልዶ በጠዋት በአንተው እጅ ነቅቶ መዋል ደጅ እየጠኑ

ዓይኔን ጉዳዬ ላይ ማድረግ
ፍለጋዬን እድሜ ልክ መፈለግ
ናፍቆቴን ሳላርፍ መናፈቅ
ጉጉቴን ሳልደክም መፈለግ
እንዲሆንልኝ ይብዛልኝ ጸጋህ
ጊዜው ደርሶ እስክደርስ አንተ ጋር
ገባ ወጣ እግሬ ሳይልብኝ
ፍለጋዬ ሳትጎድል ብዛልኝ

በድነቴ ጠዋት በገባኸኝ ማግስት
ጨዋታ ወሬዬ መወደዴን ማድነቅ
ዘምሬህ አልጠግብ አውርቼህ አልረካ
ይህቺ ትንሽ ልቤ ለፍቅርህ ሸፍታ

አልደግ አንተ ላይ እራሴን አልቻል
አጓጉል ነው ሁሉም ያላንተ መች ያምራል
መጠበቂያ አጥሬ መሰንበቻዬ ነህ
ልኑር እንደፈዘዝሁ ዓይኔ አንተን እያለ

ጉዳዬ አንተው
መናፈቄ መምጣትህ
ጉጉቴ ዓይኔ እስከሚያይህ

ሁሌ ሁሌ ሁሌ ሁሌ አንተን ብቻ
እስከ እድሜዬ መቋጫ
ሁሌ ሁሌ ሁሌ ኢየሱስን ብቻ
እስከ እድሜዬ መቋጫ

ሁሌ ሁሌ ሁሌ ሁሌ አንተን ብቻ
እስከ እድሜዬ መቋጫ
ሁሌ ሁሌ ሁሌ ሁሌ አንተን ብቻ
እስከ እድሜዬ መቋጫ

አይኔን ጉዳዬ ላይ ማድረግ
ፍለጋዬን እድሜ ልክ መፈለግ
ናፍቆቴን ሳላርፍ መናፈቅ
ጉጉቴን ሳልደክም መፈለግ
እንዲሆንልኝ ይብዛልኝ ጸጋህ
ጊዜው ደርሶ እስክደርስ አንተ ጋ
ገባ ወጣ እግሬ ሳይልብኝ
ፍለጋዬ ሳትጎድል ብዛልኝ