ፍለጋው አደረገኝ (Filegaw Aderegegn) - አስቴር ፡ አበበ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አስቴር ፡ አበበ
(Aster Abebe)

Aster Abebe 2.png


(2)

ሃሌሉያ
(Hallelujah)

ዓ.ም. (Year):
"፳፪፬" is not in the list (፲ ፱ ፻ ፹ ፩, ፲ ፱ ፻ ፹ ፪, ፲ ፱ ፻ ፹ ፫, ፲ ፱ ፻ ፹ ፬, ፲ ፱ ፻ ፹ ፭, ፲ ፱ ፻ ፹ ፮, ፲ ፱ ፻ ፹ ፯, ፲ ፱ ፻ ፹ ፰, ፲ ፱ ፻ ፹ ፱, ፲ ፱ ፻ ፺ ፩, ...) of allowed values for the "ዓመተምህረት" property.
(2024)
ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ አበበ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Abebe)

እንደገናን ፡ ባያውቅ ፡ ዳግም ፡ ዕድል ፡ ባይሰጥ
ማን ፡ ይችል ፡ ነበረ ፡ የጌታን ፡ ደጅ ፡ ሊረግጥ
እየተደገፈ ፡ በማይሰፈር ፡ ፀጋው
እንደኔ ፡ የቆመ ፡ ስንቱን ፡ ቤት ፡ ይቁጠረው
ስንቱን ፡ ቤት ፡ ይቁጠረው (፪x)

ደጋግሞ ፡ የተፈተነ ፡ እምነቴ
እንዳይንኮታኮት ፡ አልቆለት ፡ እንዳይወድቅ
እንደስንዴ ፡ ሊያበጥረኝ ፡ የወጣውን ፡ ፈታኝ
በ ፡ ‘አይቻልም’ ፡ ሲሰድ

የአንደበቴን ፡ ሳይሆን ፡ ያወቀ ፡ የልቤን
እንደተመኘሁት ፡ ልሆን ፡ ያለመቻሌን
እስኪቆሙ ፡ እግሮቼ ፡ በብዙ ፡ አገዘኝ
ሃይልን ፡ እስክቀበል ፡ አይዞሽ ፡ በርቺ ፡ እያለኝ
ያለቀልኝ ፡ መስሎት ፡ ለሳቀብኝ ፡ ጠላቱ
ማልዶ ፡ ማለደልኝ ፡ ጉልበቴን ፡ አጸናት (፪x)

ክህደት ፡ መሃላዬን ፡ አላውቀውም ፡ ማለቴን
ዶሮ ፡ ሶስቴ ፡ እስኪጮህ ፡ አልፎ ፡ መጨመሬን
ከትንሳኤው ፡ ማግስት ፡ ብርቱዎች ፡ እያሉ
ከሰነፎች ፡ ተርታ ፡ እንደኔ ፡ ያልዋሉ
ፍልጋው ፡ አረገኝ ፡ መጣ ፡ ወዳለሁበት
ሊቀጥለኝ ፡ ዳግም ፡ ከተቆረጥኩበት
ፍለጋው ፡ አደረገኝ ፡ መጣ ፡ ወዳለሁበት (፬x)

በማይጠቅሙት ፡ መጠቀም ፡ ልማዱ ፡ ለሆነው
በማለዳ ፡ ምስጋናዬ ፡ ይኸው
በማይጠቅሙት ፡ መጠቀም ፡ ልማዱ ፡ ለሆነው
ለተቤዠኝ ፡ ምስጋናዬ ፡ ይኸው
በማይጠቅሙት ፡ መጠቀም ፡ ልማዱ ፡ ለሆነው
ሳላቋርጥ ፡ ምስጋናዬ ፡ ይኸው

በትንሽ ፡ አዕምሮዬ ፡ ስላሰብኩት ፡ ነገር
ብዕሬን ፡ ይዣለው ፡ ቃላትን ፡ ቀምሬ ፡ በዜማ ፡ ልናገር
አልችልም ፡ ልደብቅ ፡ የውስጥ ፡ ደስታዬን
እሱ ፡ በኔ ፡ ሆኖ ፡ ነውሬን ፡ አስወግዶ ፡ ከሰው ፡ መቆጠሬን
ዝም ፡ ይባላል ፡ እንዴ ፡ ደግሞስ ፡ ያስችላል ፡ ወይ
አትረፍርፎ ፡ አድርጎልኝ ፡ ረድኤቱን ፡ ከላይ
የቃላትን ፡ ድንበር ፡ ጥሶ ፡ ያለፈ ፡ መውደድ
አንድ ፡ ልጁን ፡ ሰጥቶ ፡ የራሱ ፡ የሚያደርግ

አጽናንቶኛል ፡ ባድማ ፡ ህይወቴን ፡ በመልካምነቱ ፡ ሞልቶ
አስደሰተኝ ፡ በረሃ ፡ ህይወቴን ፡ እንደ ፡ ኤደን ፡ አድርጎ
ተድላ ፡ አደለኝ ፡ የደስታ ፡ የቅኔ ፡ ድምጽ ፡ ወጣ ፡ ከቤቴ
መራቄ ፡ ቀርቶ ፡ ቀርቤአለሁ ፡ አብ ፡ ሆኖኝ ፡ አባቴ (፪x)

በትንሽ ፡ አዕምሮዬ ፡ ስላሰብኩት ፡ ነገር
ብዕሬን ፡ ይዣለው ፡ ቃላትን ፡ ቀምሬ ፡ በዜማ ፡ ልናገር
አልችልም ፡ ልደብቅ ፡ የውስጥ ፡ ደስታዬን
እሱ ፡ በኔ ፡ ሆኖ ፡ ነውሬን ፡ አስወግዶ ፡ ከሰው ፡ መቆጠሬን
ዝም ፡ ይባላል ፡ እንዴ ፡ ደግሞስ ፡ ያስችላል ፡ ወይ
አትረፍርፎ ፡ አድርጎልኝ ፡ ረድኤቱን ፡ ከላይ
የቃላትን ፡ ድንበር ፡ ጥሶ ፡ ያለፈ ፡ መውደድ
አንድ ፡ ልጁን ፡ ሰጥቶ ፡ የራሱ ፡ የሚያደርግ