From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
አስቴር ፡ አበበ (Aster Abebe)
|
|
፪ (2)
|
ሃሌሉያ (Hallelujah)
|
ዓ.ም. (Year):
|
"፳፪፬" is not in the list (፲ ፱ ፻ ፹ ፩, ፲ ፱ ፻ ፹ ፪, ፲ ፱ ፻ ፹ ፫, ፲ ፱ ፻ ፹ ፬, ፲ ፱ ፻ ፹ ፭, ፲ ፱ ፻ ፹ ፮, ፲ ፱ ፻ ፹ ፯, ፲ ፱ ፻ ፹ ፰, ፲ ፱ ፻ ፹ ፱, ፲ ፱ ፻ ፺ ፩, ...) of allowed values for the "ዓመተምህረት" property. (2024)
|
ቁጥር (Track):
|
፩ (1)
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የአስቴር ፡ አበበ ፡ አልበሞች (Albums by Aster Abebe)
|
|
ደረበልኝ ፡ በላይ ፡ አለበሰኝ ፡ ጸጋ
እንዲሆነኝ ፡ አቅም ፡ እስክደርስ ፡ እርሱ ፡ ጋር
በአቅመኞች ፡ ጉልበት ፡ በብርቱዎች ፡ ማደም
የማትገፈፍ ፡ ልብሴ ፡ ለኔ ፡ እንዳንተ ፡ የለም (፪x)
በህብሮች ፡ ቀለም ፡ በተንቆጠቆጠች
ከወንድሞች ፡ መሃል ፡ ለዮሴፍ ፡ ለተባለች
ቢውልባት ፡ ደምቆ ፡ ለብሶ ፡ ቢያምርበት
ቢያሳብቅ ፡ ሞገሱን ፡ አይንህ ፡ እንዳረፈበት
ዛቻ ፡ ሲጠብቀው ፡ መልካም ፡ እያሰበ
እንጀራ ፡ አቀብሎ ፡ ጉድጓድ ፡ ለተቸረ
ለሰው ፡ ሃገር ፡ ሰው ፡ ጠብቀህ ፡ ዘመንን
በአንተው ፡ እጅ ፡ ለበሰ ፡ የማይገፈፈውን
የንጉስ ፡ ልብ ፡ ከፍቶ ፡ ጦርን ፡ ሲወረውር
የተቀባው ፡ ቅባት ፡ ሲያስነሳ ፡ ስደትን
በእባብ ፡ ጊንጥ ፡ መኖሪያ ፡ በአዶላም ፡ ዋሻ
ስንቱን ፡ አስጀገነ ፡ ሆነኸው ፡ ድል ፡ መንሻ
መጠጊያ ፡ ለሌለው ፡ ማስገቢያ ፡ ለአንገቱ
ስንቱ ፡ ተማምኖብህ ፡ ተረፈ ፡ ለስንቱ
ሸለቆው ፡ ጠገበ ፡ በጠልህ ፡ ረስርሶ
ቀን ፡ እስኪወጣለት ፡ አንተን ፡ ተንተርሶ
ፈራ ፡ ፍርሃቴ ፡ ቃልህን ፡ ስትናገር
ሸሸ ፡ ጨለማዬ ፡ ነጋ ፡ በእኔ ፡ መንደር
ጥንካሬ ፡ አገኘኝ ፡ ፊትህን ፡ በማየት
ደመቀ ፡ ህይወቴ ፡ ከአንተ ፡ በመቆየት ፡ አዎ (፪x)
ከላይ ፡ ከውሽንፍር ፡ ጥላ ፡ ከሃሩሩ
የጸናልኝ ፡ ቤቴ ፡ መርከብ ፡ በማዕበሉ
የማይደፈር ፡ አጥር ፡ ለጎመጀኝ ፡ አውሬ
ትልቁን ፡ ወግድ ፡ ባይ ፡ የማይነቀነቅ ፡ በሬ (፪x)
አዎ ፡ ስምህ ፡ ነው ፡ አዎ (፬x)
ምን ፡ ይሆናል ፡ ለጸጋው ፡ ታልፎ ፡ የተሰጠ
መንገድ ፡ ጎዳናውን ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይኸውልህ ፡ ያለ (፪x)
ያየህለት ፡ እንጂ ፡ የሚያልፍ ፡ የሚያገድመው ፡ አያገኘው
ቃሉ ፡ እንዳለ ፡ እንደተጻፈለት ፡ ነው ፡ የሚኖረው (፪x)
ምን ፡ ይሆናል ፡ ለጸጋው ፡ ታልፎ ፡ የተሰጠ
መንገድ ፡ ጎዳናውን ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይኸውልህ ፡ ያለ (፪x)
ያየህለት ፡ እንጂ ፡ የሚያልፍ ፡ የሚያገድመው ፡ አያገኘው
ቃሉ ፡ እንዳለ ፡ እንደተጻፈለት ፡ ነው ፡ የሚኖረው (፪x)
አዎ ፡ ስምህ ፡ ነው ፡ አዎ (፬x)
|