Aster Abebe/Hallelujah/Eredashalehu
{{Lyrics |ዘማሪ=አስቴር ፡ አበበ |Artist=Aster Abebe |ርዕስ=እረዳሻለሁ |Title=Eredashalehu |አልበም=ሃሌሉያ |Album=Hallelujah |Volume=2 |Year=2024 |Track=7 |ቋንቋ=አማርኛ |Language=Amharic
ውጪ ብሎ አስወጥቶኝ ከኖርኩበት ቀዬ ሰፈር ሊሰራብኝ ገንዘብ ሊያደርገኝ ለእርሱ ስራ ለእርሱ ክብር ከዳር ማድረስ ሳይችል ቀርቶ ጥሎኝ አይሄድ በበረሀ የአመንኩትን አውቀዋለሁ አይቼዋለሁኝ ትናንትና (፫) ለነገም አመንኩት ልቤ በእርሱ ፀና ልቤ እርሱ ጋር ፀና (፰) ትናንት ሲደግፈኝ አይቻለሁና ልቤ እርሱ ጋር ፀና ያለኝ እውነት ሆኖ እያለ መልካምነቱንም ፍጥረት እያወቀ እንደተረሳሁ እንደተወኝ እንደማያየኝ እንደጣለኝ ያ ክፉ ጠላቴ ብዙ ብዙ ዋሽቶኛል እውነታውን ግን ቃለ ነግሮኛል (፪) እረዳሻለሁ አግዝሻለሁ በፀናች ክንዴ እደግፍሻለሁ ልብሽ ቤቴ ነው የኔ የአንቺ ነው ለአንቺ ያለኝ ፍቅር ጥልቅ ነው ሁኔታ የሚለው ሌላ ሌላ ነው ቃሉ ያለኝ ግን በርቺ ነው
(፪)
እረዳሃለሁ... ጠላቴ ያለው ሁሉ ውሸት ነው ጌታ(ቃሉ)
ያለኝ ግን እውነት ነው
እቀጥላለሁ ገና እሄዳለሁ እጁ ይዞኛል (ተሸክሞኛል) ምን እሆናለሁ ብዙ ብዙ መልካም ነገር ብዙ ብዙ በጎ ነገር ብዙ ብዙ ጥሩ ነገር ትናንቴ ላይ አርጎልኛል አመሰግነዋለሁ (፬) ቅኔዬ አልሻገተ ትውልድ አላለፈው ገና በልጅነት በልቤ ያኖረው ከአፉ በወጣው ቃል የተፃፈ ነገር እርጅና አያውቀውም ይህ ሰማይ ይናገር አይቼዋለሁኝ ትናንትና...