From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አንተ ፡ የሌለህበት ፡ ቦታ ፡ ለምኔ
ሃገር ፡ ለምኔ ፡ ከፍታ ፡ ለምኔ
አንተ ፡ የሌለህበት ፡ ህብረት ፡ ለምኔ
መዝሙር ፡ ለምኔ ፡ ወሬ ፡ ለምኔ (፪x)
አስጠጋኝ ፡ ወደ ፡ እቅድህ
ወዳየህልኝ ፡ ወደ ፡ ሃሳብህ (፪x)
የእግሮቼን ፡ ጉዞ ፡ መትርልኝ
የአንደበቴን ፡ ቃል ፡ ስፈርልኝ
ለፈቃዴ ፡ ገደብን ፡ አብጅለት
ሞገደኛው ፡ ልቤ ፡ ይወቅ ፡ ለከት
አስተምረኝ ፡ ምን ፡ ትላለህ ፡ ማለት (፪x)
አይኖቼ ፡ እያዩ ፡ ቅጥቅጧን ፡ ሸንበቆ ፡ ደግፈህ ፡ ስታቆመኝ
እያወቀ ፡ ልቤ ፡ የምጤሰውን ፡ ጧፍ ፡ ቀርበህ ፡ ስታበራኝ
ጆሮዬ ፡ እየሰማ ፡ ለራስ ፡ ማልበቃውን ፡ ስታተርፈኝ ፡ ለሃገር
በቀረልኝ ፡ እድሜ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ውጪ ፡ አፌ ፡ ምን ፡ የናገር
አሁንም ፡ ብዛልኝ ፡ እንዲረዝም ፡ እድሜዬ
አብልጬ ፡ ልጠጋህ ፡ እንዲደምቅ ፡ ማታዬ
ሁነኝ ፡ መዋያዬ ፡ በቀረልኝ ፡ ዘመን
መንገዴ ፡ እየነጋ ፡ እስኪሆን ፡ ሙሉ ፡ ቀን (፪x)
ዉሎ ፡ ካንተ ፡ ጋር ፡ አድሮና ፡ ሰንብቶ
ማን ፡ በትናንት ፡ ቀረ ፡ ከአንተ ፡ ብዙ ፡ ቀድቶ
የለውጥ ፡ ጅማሬ ፡ ነህ ፡ የሕይወት ፡ ማጣፈጫ
የተጠጉህ ፡ ሁሉ ፡ ወጥተዋል ፡ በብልጫ (፪x)
ሰሞነኛ ፡ እንዳልሆን ፡ አድሮ ፡ እንዳልሰለች
ጉልበቴን ፡ ላስጠጋ ፡ ወደ ፡ ቃሎችህ ፡ ደጅ
ዘመንን ፡ ዘላቂ ፡ እንዲሆን ፡ ነገሬ
ዙረቴን ፡ አቁሜ ፡ ልፈልግህ ፡ ዛሬ
|