From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
አስቴር ፡ አበበ (Aster Abebe)
|
|
፪ (2)
|
ሃሌሉያ (Hallelujah)
|
ዓ.ም. (Year):
|
"፳፪፬" is not in the list (፲ ፱ ፻ ፹ ፩, ፲ ፱ ፻ ፹ ፪, ፲ ፱ ፻ ፹ ፫, ፲ ፱ ፻ ፹ ፬, ፲ ፱ ፻ ፹ ፭, ፲ ፱ ፻ ፹ ፮, ፲ ፱ ፻ ፹ ፯, ፲ ፱ ፻ ፹ ፰, ፲ ፱ ፻ ፹ ፱, ፲ ፱ ፻ ፺ ፩, ...) of allowed values for the "ዓመተምህረት" property. (2024)
|
ቁጥር (Track):
|
፫ (3)
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የአስቴር ፡ አበበ ፡ አልበሞች (Albums by Aster Abebe)
|
|
እንደገና ፡ ረሃብ ፡ እንደገና ፡ ጥማት
ትናንት ፡ ምንም ፡ እንዳላየ
እንደገና ፡ ናፍቆት ፡ እንደገና ፡ ጉጉት
አንተ ፡ ወዳለህበት (፪x)
ጥቂት ፡ አንተን ፡ ቀምሶ ፡ እንደ ፡ ጠገበ ፡ ሰው
መሆን ፡ የጤና ፡ አይደለም ፡ ረሃቤን ፡ ፈውሰው
ጥቂት ፡ አንተን ፡ ቀምሶ ፡ እንደ ፡ ጠገበ ፡ ሰው
መሆን ፡ የጤና ፡ አይደለም ፡ ረሃቤን ፡ ፈውሰው
ዕለት ፡ ዕለት ፡ ባዶ ፡ ትሁንና ፡ ነፍሴ
በመገኘትህ ፡ ውስጥ ፡ ይረስርስ ፡ መንፈሴ (፪x)
በቃኝ ፡ የማልለው ፡ ይለፈኝ ፡ የማልለው
ሰለቸኝ ፡ የማልለው ፡ ያንተ ፡ ሕልውናህ
ደስታዬ ፡ ያለበት ፡ ያለፈ ፡ ሰላሜ
መገኘትህ ፡ ነው ፡ መዋያ ፡ ማደሪያዬ
ናና ፡ እስኪ ፡ አጠጣኝ
ናና ፡ እስኪ ፡ አጉርሰኝ
የእጅህን ፡ ሳይሆን ፡ ክብር ፡ መልክህን
የምድሩን ፡ ሳይሆን ፡ ሕልውናህን
ሌላውን ፡ ሳይሆን ፡ አንተው ፡ እራስህን
ናና ፡ እስኪ ፡ አጠጣኝ
ናና ፡ እስኪ ፡ አጉርሰኝ
የእጅህን ፡ ሳይሆን ፡ ክብር ፡ መልክህን
የምድሩን ፡ ሳይሆን ፡ በላይ ፡ ያለውን
ሌላውን ፡ ሳይሆን ፡ አንተው ፡ እራስህን
የፊትህን ፡ ሳይሆን ፡ ፈልጎ ፡ የእጅህን
ባትገባም ፡ ከቤቴ ፡ ላክ ፡ ብቻ ፡ ቃልህን
የእምነቱን ፡ ቁመት ፡ አድንቀህ ፡ እንዳለፍከው
አንተን ፡ በደጅ ፡ ትቶ ፡ ፈውሱን ፡ ብቻ ፡ እንዳለው
አይደል ፡ መገስገሴ ፡ ፊትህን ፡ ማለቴ
ማድጋዬን ፡ ልሞላ ፡ ላሰማምር ፡ ቤቴን
ይህን ፡ ሁሉ ፡ እንዳለ ፡ ክነዝብርቅርቁ
ካንተ ፡ ካልከተመኝ ፡ ካቆመኝ ፡ በሩቁ
ሳበኝ ፡ በእጆችህ ፡ ወደ ፡ ክብርህ ፡ ጥልቅ
አስገባኝ ፡ ከእልፍኝህ ፡ ጅምሩም ፡ ባያልቅ
በቃኝ ፡ የማልለው ፡ ይለፈኝ ፡ የማልለው
ሰለቸኝ ፡ የማልለው ፡ ያንተ ፡ ሕልውናህ
ደስታዬ ፡ ያለበት ፡ ያለፈ ፡ ሰላሜ
መገኘትህ ፡ ነው ፡ መዋያ ፡ ማደሪያዬ (፪x)
|