From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
አስቴር ፡ አበበ (Aster Abebe)
|
|
፪ (2)
|
ሃሌሉያ (Hallelujah)
|
ዓ.ም. (Year):
|
"፳፪፬" is not in the list (፲ ፱ ፻ ፹ ፩, ፲ ፱ ፻ ፹ ፪, ፲ ፱ ፻ ፹ ፫, ፲ ፱ ፻ ፹ ፬, ፲ ፱ ፻ ፹ ፭, ፲ ፱ ፻ ፹ ፮, ፲ ፱ ፻ ፹ ፯, ፲ ፱ ፻ ፹ ፰, ፲ ፱ ፻ ፹ ፱, ፲ ፱ ፻ ፺ ፩, ...) of allowed values for the "ዓመተምህረት" property. (2024)
|
ቁጥር (Track):
|
፮ (6)
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የአስቴር ፡ አበበ ፡ አልበሞች (Albums by Aster Abebe)
|
|
እረሳሁት ፡ ጥያቄዬን
የከበበኝን ፡ በዙሪያዬ
ስቀርብ ፡ ፊትህ ፡ ለማመስገን
ቀሎ ፡ ታየኝ ፡ ሁሉም ፡ ነገር (፪x)
ሳላመልክህ ፡ ጊዜው ፡ አይለፍ
የሚገባህን ፡ ምስጋና ፡ ሳላቀርብ
ሞልቶ ፡ ላይሞላ ፡ የምድሩ ፡ ነገር
ካልክልኝ ፡ አልጎድልም ፡ ለጭንቅ ፡ ውሎ ፡ ማደር
ርቋል ፡ ከኔ ፡ ሰፈር (፪x)
አመልክሃለው (፫x) ፡ በማደሪያዎችህ ፡ መካከል ፡ ቆሜ
አመልክሃለው (፫x) ፡ በማደሪያዎችህ ፡ መካከል ፡ ቆሜ
ለተራራው ፡ ቁመት ፡ እያልኩኝ ፡ ትልቅ ፡ ነህ
ለሸለቆው ፡ ጥልቀት ፡ እያልኩኝ ፡ ሙላት ፡ ነህ
ለሞገዱ ፡ ብርታት ፡ እያልኩኝ ፡ ሰላም ፡ ነህ
ለጨለማው ፡ ርዝመት ፡ እያልኩኝ ፡ ብርሃን ፡ ነህ
አመልክሃለው (፫x) ፡ በማደሪያዎችህ ፡ መካከል ፡ ቆሜ
ብዙ ፡ ጊዜ ፡ ታገልኩ ፡ ከቃላቶች ፡ ጋራ
ስላንተ ፡ ማንነት ፡ በዝርዝር ፡ ላወራ
አንሰው ፡ ተገኙብኝ ፡ ያለኝ ፡ ሁሉ ፡ አላረካኝ
እንደገባኝ ፡ መጠን ፡ እንኳን ፡ ልገልጽህ ፡ አቃተኝ (፪x)
ማንም ፡ እንደሚልህ ፡ አይደለህም
ከመታወቅ ፡ ታልፋለህ
እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ (፪x)
ትልቅ ፡ ነህ (፪x) ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ (፬x)
ካነበብኩት ፡ አይደል ፡ ከሰው ፡ የሰማሁት
ዛሬ ፡ በዚህ ፡ ሰዓት ፡ ፊትህ ፡ ያመጣሁት
ከነፍሴ ፡ ምስጋና ፡ ከውስጠቷ ፡ የሆነ
አፌን ፡ ሞልቶ ፡ የሚፈስ ፡ አዲስ ፡ ቅኔ ፡ አለ (፪x)
ያላነሰ ፡ ያላጠረ
ከላይ ፡ ከላይ ፡ ያልሆነ
ለእኔ ፡ ፍቅር ፡ ለኢየሱሴ
አለኝ ፡ ምስጋና ፡ ከነፍሴ (፪x)
|