የነፍሴ ፡ ምርጫ (Yenefse Mircha) - አስራት ፡ ሙላቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስራት ፡ ሙላቸው
(Asrat Mulachew)

Asrat Mulachew 2.jpg


(2)

ሕይወትህ ፡ ሕይወቴ
(Hiwoteh Hiwotie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፱ (2017)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 4:55
ጸሐፊ (Writer): አስራት
(Asrat M.
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስራት ፡ ሙላቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Asrat Mulachew)

መቼም ብዙ - ብዙ አማልክትና ብዙ ጌቶች አሉ
በባህሪያቸው አማልክት ሳይሆኑ አምላክ ነን የሚሉ
ከማንም/ከየቱም ጋር ሳታነፃፅርህ ሳታወዳድርህ
ነፍሴ ወዳህ በላይዋ ሾመችህ አንተን እግዚአብሄር
                 የነፍሴ ምርጫ ነህ የነፍሴ /2
                 የቤቴ ምርጫ ነህ የቤቴ/2

መቼም ኑሮ አይሞላ ቢለፋ ቢደከም
አንተ የሌለህበት ሩጫ ዋጋ የለውም/ሩጫም አያረካም
ፅድቅህን የፈለገ መንግስትህን ያለ
እርሱ ነው በሰማይ በምድር የታደለ

የነገሮች መሙላት የነገሮች መጉደል
ለመስፈርት አይቀርብም አንተን ለመከተል
ከብዙ ዕልፍ መሃል የተመረጥክ ነህ
ልክ እንደአባቶቼ ለኔም ምርጫዬ ነህ
                 የነፍሴ ምርጫ ነህ የነፍሴ /2
                 የቤቴ ምርጫ ነህ የቤቴ/2
የሁሉ ጌታ ነህ ምርጫዬ ያረኩህ
ያዋጣኛል ብዬ የተከተልኩህ
ለሰማዩ ቤቴ ዋስትና ከሆንከኝ
እኔ ለምን ልፍራ በምድር እያለሁኝ

የነገሮች መሙላት የነገሮች መጉደል
ለመስፈርት አይቀርብም አንተን ለመከተል
ከብዙ ዕልፍ መሃል የተመረጥክ ነህ
ልክ እንደሌሎቹ ለኔም ምርጫዬ ነህ
                 የነፍሴ ምርጫ ነህ የነፍሴ /2
                 የቤቴ ምርጫ ነህ የቤቴ/2
ምርጫዬ ነህ /2/ እኔና ቤቴ ምናመልክህ
ምርጫዬ ነህ /2/ በኔና በቤቴ የምትመለክ