From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
መርገም ተሰበረ ቀንበር ተወገደ የምስራች ሆነ
ፍርድም ተቀየረ አበሳችን ቀረ አህዛብም ዳነ
በዳዊት ከተማ መድሃኒት የሆነ ጌታ ተወለደ
ተጨንቃ ላለችው ለተቸገረችው ከሰማይ ወረደ
ለዚህ ነው ደስ ያለን /2/ ከሰማይ የሆነ አዳኝ ስላገኘን
ዛሬ የምስራች ተሰማ
ዛሬ በዳዊተ ከተማ
ዛሬ ከዕለታት ባንዱ ቀን ዛሬ (ሰማን መልካም ወሬ)
መድሃኒት ክርስቶስ መጣ ጌታ
ለህዝብ ሁሉ ሆነ ታላቅ ደስታ
ነፍሱ ብርሃን ሳታይ በሰይጣን እስራት ነፃነትን ላጣ
ተስፋ ቆርጦ ያለን የሚቅበዘበዝን አርነት ሚያወጣ
በቤተልሄም ከታላላቆች ዘንድ ስፍራ ሳይታጣ
ንጉስ ቤት ሲጠበቅ ሁሉን ሊያድን ወዶ ጌታ ከታች መጣ
ለዚህ ነው ደስ ያለን /2/ ከሰማይ የሆነ አዳኝ ስላገኘን
በጨለማ ሀገር በሞት ጥላ ሳለን ብርሃንህ በራ
ህፃን ተወለደ ደህንነት ሚያመጣ የእግዚአብሄር ስራ
ዘመኑ ደረሰ ድንግልም ፀነሰች ወንድ ልጅ ወለደች
ድንቅ መካር ሃያል አምላክ ስላገኘች ምድር እልል አለች
ለዚህ ነው ደስ ያለን /2/ ከሰማይ የሆነ አዳኝ ስላገኘን
ስሙ ነው ድንቅ መካር / ሃያል አምላክ / የዘላለም አባት / የሰላም ዓለቃ / ስሙ ነው
እረኞች ድምፅ ሰሙ መንጋ ሲጠብቁ ያደሩ በሜዳ
በደስታ ዘለሉ የምስራች ሰምተው ድንግሊቱ ወልዳ
ሊቃውንት ወደዱ ሊሰግዱለት መጡ በብዙ እልልታ
ክብር በአርያም ለእግዚአብሄር ሆነ ለሰው ልጆች ደስታ
ለዚህ ነው ደስ ያለን /2/ ከሰማይ የሆነ አዳኝ ስላገኘን
|