ይግባ ፡ ከቤቱ (Yegba Kebietu) - አስራት ፡ ሙላቸው

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አስራት ፡ ሙላቸው
(Asrat Mulachew)

Asrat Mulachew 2.jpg


(2)

ሕይወትህ ፡ ሕይወቴ
(Hiwoteh Hiwotie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፱ (2017)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 6:54
ጸሐፊ (Writer): አስራት
(Asrat M.
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስራት ፡ ሙላቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Asrat Mulachew)

በሮች ይከፈቱ /2/ የክብር ንጉስ ይግባ ከቤቱ /4/
በሮች ይከፈቱ /2/ ጌታው ኢየሱስ ይግባ ከቤቱ /4/
በሮች ይከፈቱ የሃያላኑ የነገስታቱ
በሮች ይከፈቱ የብርቱዎቹ የመኳንንቱ
የክብር ንጉስ ይግባ ከቤቱ
ጌታው ኢየሱስ ይግባ ከቤቱ

የክብር ንጉስ ነህ ልቤ የሚገባህ
        የነገስታት ንጉስ ነህ ልዩ ስፍራ የሚሰጥህ
        ህይወቴን ላንተ አቀርባለሁ - ወዳንተ መቅረብ መርጫለሁ
        ዘመኔን ግዛው ያንተ አድርገው

አያምርብኝም ያላንተ - አይሆንልኝም ያላንተ
ከደጁ ቆመህ ውበቴ - ገፍቼ አውጥቼህ ከቤቴ
      ግባልኝ /4/ ያንተ ነው ቤቱ /4/
     ኑርልኝ /4/ ያንተ ነው ቤቱ /4/

የህይወት ውሃ አንተን መርሳቴ
ካዘዝከኝ መንገድ ፈቀቅ ማለቴ
ለጥቅሜ እንዳይሆን ተረድቻለሁ
የክብር ልብሴን አውልቄ ሳለሁ
        ህይወት ያላንተ ምን ትርጉም አለው
        ቤቴ ግባና ኑሮን ልኑረው

ከቀድሞው ክፋት ያሁኑ ይባስ
የውሃ ጉድጓድ መቆፈር ለራስ
ያገኘሁ መስሎኝ ባጠልቅ ልቀዳ
ጉድጓዱ እንደሁ ሙሉ ቀዳዳ
       ህይወት ያላንተ ምን ትርጉም አለው
       ቤቴ ግባና ኑሮን ልኑረው

ከደጄ ቆመህ ስታንኳኳ አሃሃ ድምፅህን ሰምቼ
እንዳልከፍትልህ በብዙ እንግዶች አሃሃ ቤቴን ሞልቼ
በዚህ አልቀጥልም ዛሬ ግን አንተን አሃሃ ፈልግሃለሁ
ውዴን ከቤቱ ገፍተው ያስወጡትን አሃሃ አባርራለሁ
           ዋላ የውሃ ምንጭ ስትናፍቅ ስላየች
           ነፍሴ አንተን /3/ ብቻ አለች