ይችላል (Yechelal) - አስራት ፡ ሙላቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስራት ፡ ሙላቸው
(Asrat Mulachew)

Asrat Mulachew 2.jpg


(2)

ሕይወትህ ፡ ሕይወቴ
(Hiwoteh Hiwotie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፱ (2017)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 5:36
ጸሐፊ (Writer): አስራት
(Asrat M.
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስራት ፡ ሙላቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Asrat Mulachew)

ይችላል /4/ ድንቅና ታምራት ብቻውን ያደርጋል
ለሰው የማይቻል ለእግዚአብሄር ይቻላል

ሃኪም ያቃተውን ደዌ ይፈውሳል - እግዚአብሔር ይችላል
ህዝብን ያናወጠን ማዕበል ይገስፃል - እግዚአብሔር ይችላል
እርኩስ መንፈስ ፊቱ መች ችሎ ይቆማል - እግዚአብሔር ይችላል
ለኢየሱስ ክብር ወድቆ ይንበረከካል - እግዚአብሔር ይችላል

            ይችላል /2/ እግዚአብሄር ይችላል
           ድንቅና ታምራት ብቻውን ያደርጋል
           ድንቅና ታምራት ብቻውን ያደርጋል
           ለሰው የማይቻል ለእግዚአብሄር ይቻላል


ነፋስን ይጠራል ባህር ዝም ያሰኛል - እግዚአብሔር ይችላል
የተፍገመገመን አፅንቶ ያቆማል - እግዚአብሔር ይችላል
አለትን ሰንጥቆ ጥማትን ያረካል - እግዚአብሔር ይችላል
ጥቂት ባርኮ አብልቶ ሺሁን ያበረታል - እግዚአብሔር ይችላል

ተራራውን ንዶ ደልዳላ ያደርጋል - እግዚአብሔር ይችላል
ደረቁን ሸለቆ በውሃ ይሞላል - እግዚአብሔር ይችላል
መንፈሱን ያፈሳል ህይወትን ያድሳል - እግዚአብሔር ይችላል
ሳይታክት ለሚጮህ እግዚአብሄር ይመጣል - እግዚአብሔር ይችላል

ዕውርን ያበራል ሽባን ያዘልላል - እግዚአብሔር ይችላል
እንቆቅልሽ ፈቶ ቋጠሮ ይበጥሳል - እግዚአብሔር ይችላል
ለሞተው ማንነት ህይወትን ይሰጣል - እግዚአብሔር ይችላል
ዛሬም ለሚታመን አምላኬ ይችላል - እግዚአብሔር ይችላል