የኢየሱስ ፡ መንፈስ (YeIyesus Menfes) - አስራት ፡ ሙላቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስራት ፡ ሙላቸው
(Asrat Mulachew)

Asrat Mulachew 2.jpg


(2)

ሕይወትህ ፡ ሕይወቴ
(Hiwoteh Hiwotie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፱ (2017)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 4:37
ጸሐፊ (Writer): አስራት
(Asrat M.
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስራት ፡ ሙላቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Asrat Mulachew)

እኔ ስዘምር እጆቼን ሳነሳ
ኢየሱስ እያልኩኝ ስሙን ሳነሳሳ
ምን እያልኩ እንደሆን ያልገባው ሰው ካለ - አንድ ነገር አለ
ያዘመረኝ ደስተኛ ያረገኝ የኢየሱስ መንፈስ ነው /2/
ያዘመረኝ ደስተኛ ያረገኝ መንፈሱ አግኝቶኝ/ነክቶኝ መንፈስ ነው /2/
                        መንፈሱ አግኝቶኝ/ነክቶኝ /2/ እየዳሰሰኝ እያዘመረኝ

ምን ያዘምረዋል ለምንስ ይጮሃል
ምንስ የተለየ ነገር አግኝቶታል
ብሎ ለሚጠይቅ ነገሩ ላልገባው - ምክንያቴ አንድ ነው
ያዘመረኝ ነፃነት የሰኝ የኢየሱስ መንፈስ ነው /2/
ያዘመረኝ ፈትቶ የለቀቀኝ የኢየሱስ መንፈስ ነው /2/
                       መንፈሱ አግኝቶኝ/ነክቶኝ /2/ እያስደሰተኝ - እያዘመረኝ

ምህረቱ መች አልቆ ዝማሬውስ ያልቃል
መንፈሱ መች ርቆ አምልኮው ይጎድላል
የደስታዬ ምክንያት ሆኖ አግኝቼዋለሁ - ለርሱ እዘምራለሁ
ቀንም ማታ ስራዬ ይሄ ነው ለርሱ መዘመር ነው /2/
ዛሬም ነገም ስራዬ ይሄ ነው ለርሱ መዘመር ነው /2/

       ቀንም ማታ ስራዬን ሰራለሁ ላንተ ዘምራለሁ
       ዛሬም ነገም ስራዬን ሰራለሁ ላንተ ዘምራለሁ

       ቀንም ማታም ዝማሬ ላንተ ነው ደስታዬ ለሆንከው
ለዘላለም ዝማሬ ላንተ ነው አፅናኜ ለሆንከው
                    እየዳሰሰኝ እያዘመረኝእያዘመረኝ እየዳሰሰኝ