ቃልህን ፡ ላክ (Qalehen Lak) - አስራት ፡ ሙላቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስራት ፡ ሙላቸው
(Asrat Mulachew)

Asrat Mulachew 2.jpg


(2)

ሕይወትህ ፡ ሕይወቴ
(Hiwoteh Hiwotie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፱ (2017)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 4:57
ጸሐፊ (Writer): አስራት
(Asrat M.
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስራት ፡ ሙላቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Asrat Mulachew)

ቃልህን ላክ ድምፅህን ላክ -
የሰማይ አምላክ ጉባዔያችንን ባርክ
መንፈስህን ላክ እጅህን ላክ
የሰማይ አምላክ ጉባዔያችንን ባርክ

በሙታን ሸለቆ በመቃብር ላለው - ቃልህን ላክ
በድካም ደርቆ ከህይወት ለጎደለው - ድምፅህን ላክ
እስትንፋስን ሰጥተህ ህያው ልታረገው - ቃልህን ላክ
ከጉድጓድ አውጥተህ ዳግም ልታቆመው - ድምፅህን ላክ

                አዝማች

ሽባ እንዲተረተር ዕውር እንዲበራ - መንፈስህን ላክ
ድንቅ ታምራትህ ዛሬም እንዲሰራ - እጅህን ላክ
ደዌ እንዲፈወስ ቋጠሮ እንዲፈታ - መንፈስህን ላክ
አምልኮ እንዲቀርብ ለሰራዊት ጌታ - እጅህን ላክ

               አዝማች

ድንበሬን አስፋልኝ ብሎ ለለመነህ - መንፈስህን ላክ
እጅህን በላዬ ላይ አበርታልኝ ላለ - እጅህን ላክ
ሊነጋ እስኪያቅላላ ታግሎህ ለጠበቀው - እጅህን ላክ
በእውነተኛ ባርኮት እንድትገናኘው - መንፈስህን ላክ

               አዝማች

ገበናውን ደብቆ ሊያዋይህ ለመጣ - ቃልህን ላክ
እንቆቅልሽ ይዞ ፍቺውን ግን ላጣ - ድምፅህን ላክ
ያንጎዳጉድ ድምፅህ አይከልከል ከሰማይ - ቃልህን ላክ
ዛሬም እንደጥንቱ ክብርህ በዚህ ይታይ - ድምፅህን ላክ