ምህረትህ ፡ ብዙ (Meheretih Bezu) - አስራት ፡ ሙላቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስራት ፡ ሙላቸው
(Asrat Mulachew)

Asrat Mulachew 2.jpg


(2)

ሕይወትህ ፡ ሕይወቴ
(Hiwoteh Hiwotie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፱ (2017)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:45
ጸሐፊ (Writer): አስራት
(Asrat M.
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስራት ፡ ሙላቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Asrat Mulachew)

አምላኬ ምህረትህ ብዙ ነው ብዙ
ይቅርታህ ብዙ ነው ብዙ
ፍቅርህ ብዙ ነው ብዙ
ብዙ ብዙ ብዙ
              ምህረትህ/ ይቅርታህ/ ፍቅርህ/ ትዕግስትህ ብዙ ነው ብዙ
ብዙ ነው ምህረትህ/ ይቅርታህ/ ፍቅርህ/ ትዕግስትህ ብዙ ነው

እንደበደሌማ እንደ ኃጢያቴ
በፈሰሰ ነበር ቁጣህ በህይወቴ
እንደ እግዚአብሄር ፍቅር እንደምህረትህ
አለሁ እስከዛሬ አልጠፋሁ ከፊትህ
             አልሆንም እንዳልተደረገለት ሰው
             አልዋሽም በህይወቴ ባደረገው
             በብዙ ረድቶኛል ምህረትህ
             ያኖረኛል ለዘለዓለም በቤትህ

በስጋዬ ተመኝቼ ባይኔም አምሮት ተገዝቼ
ገሰገስኩኝ ብዙ ርቄ አልቀረልኝም መውደቄ
            አንተ ግን ፃድቅ ነህ አንተ ግን ይቅር ባይ
            ፈጥነህ ራራህልኝ ሁኔታዬን ስታይ
            ደግመህ ተቀበልከኝ አልተፀየፍከኝ
           በምህረትህ ብዛት ቤትህ ገባሁኝ
                       በምህረትህ ነው ጌታዬ በምህረትህ ነው
                       ቤትህ መግባቴ ጌታዬ በምህረትህ ነው
                      በምህረትህ ነው ጌታዬ በምህረትህ ነው
                       ዛሬን ማየቴ ጌታዬ በምህረትህ ነው

አይቻለሁ ምህረቱን ቀምሻለሁ ቸር መሆኑን
በየቀኑ ሁሌ አዲስ ነው ፍጥረት ሁሉ ያመስግነው
ምህረቱ ትዝ እያለው፣ ባሪያውን ካሰበው፣ ፈቅጄ አመሰግነዋለሁ