ክበርልኝ (Keberelegn) - አስራት ፡ ሙላቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስራት ፡ ሙላቸው
(Asrat Mulachew)

Asrat Mulachew 2.jpg


(2)

ሕይወትህ ፡ ሕይወቴ
(Hiwoteh Hiwotie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፱ (2017)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 5:50
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስራት ፡ ሙላቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Asrat Mulachew)

ቢልቃጡ ተሰብሮ ሽቶው ያውድህ
ነፍሴም ትገዛልህ እምባዬም ይፍሰስ
እኔ ዝቅ ልበል አንተን ከፍ ላርግህ
ክብሬን ልጣልና ክብርህን ላምጣልህ
                ክበርልኝ /8/

ያጢያተኛው ወዳጅ ነህ ሰው የራቀውን ምትጠጋ
የልቡን በር ዘልቀህ ገብተህ ጨለማውን ምታነጋ
መድኃኒት ሆንካት ለነፍሴ እስራቴን ፈታህና
በማዕድህ አስቀመጥከኝ እኔም ባንተ ታሰብኩና

              ክበርልኝ /8/

የኔ መዝሙር የኔ ዜማ የኔ ልቅሶ የኔ እምባ
ምስጋናን ቢጨምር እንጂ አንተስ ከጥንት የተቀባህ
ንግግሬ ብቻ አይደለም እርምጃዬም ያስደስትህ
እኔ ያለ ልክ ዝቅ ልበል አንተ ያለ ልክ ከፍ በል

              ቢልቃጡ ተሰብሮ....

ገና ከጥንት ስትመራኝ ስትመክረኝ አውቅሃለሁ
ዛሬ ቤቴ ልትገባ ተራ ደርሶኝ ታስቤያለሁ
ሳልወድህ እየወደድከኝ አኔ ታዲያ ምን እላለሁ
ቤቴ ባንተ ካማረልኝ ነፍሴን ፊትህ አፈሳለሁ

              ክበርልኝ /8/
          ቢልቃጡ ተሰብሮ....