ሕይወትህ ፡ ሕይወቴ (Hiwoteh Hiwotie) - አስራት ፡ ሙላቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አስራት ፡ ሙላቸው
(Asrat Mulachew)

Asrat Mulachew 2.jpg


(2)

ሕይወትህ ፡ ሕይወቴ
(Hiwoteh Hiwotie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፱ (2017)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 4:34
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስራት ፡ ሙላቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Asrat Mulachew)

kእኖራለሁ ፡ ባንተ ፡ እንቀሳቀሳለሁ
በልቼ ፡ ጠጥቼ ፡ ወጥቼ ፡ ገባለሁ
ተኝቼ ፡ ደግፈኸኝ ፡ ከእንቅልፌ ፡ ነቃለሁ
ደግሞ ፡ ባዲስ ፡ ምህረት ፡ አዲስ ፡ ቀን ፡ መራለሁ

ባንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ ፡ መኖሬ - ባንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፪x)
ባንተ ፡ ነው ፡ መሄድ ፡ መቀመጤ - ባንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ
ባንተ ፡ ነው ፡ መዋሌ ፡ ማደሬ - ባንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ
ባንተ ፡ ነው ፡ መውጣቴ ፡ መግባቴ - ባንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ
ባንተ ፡ ነው ፡ መቆም ፡ መነሳቴ - ባንተ ፡ ነው ፡ መyኖሬ

ሕይወቴ ፡ ሕይወትህ ፡ ካንተ ፡ የተቀበልኩት ፡ አለው ፡ ልዩ ፡ ትርጉም
ሕይወትህ ፡ ሕይወቴ ፡ ካንተ ፡ K ፡ በዚህ ፡ አይለካም
የሕይወት ፡ እስትንፋስ ፡ ካንተ ፡ አግኝቻለሁ
መኖር ፡ ደስ ፡ እያለኝ ፡ እንድኖር ፡ ሆኛለሁ
የሕይወት ፡ እስትንፋስ ፡ ካንተ ፡ አግኝቻለሁ
መኖሬን ፡ ወድጄው ፡ እንድኖር ፡ ሆኛለሁ

ሰሪዬ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ፈጣሪዬ ፡ መገኛዬ
የህይወት ፡ ምንጭ ፡ ነህ ፡ መኖሪያዬ
ሰሪዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ፈጣሪዬ ፡ መገኛዬ
የሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ነህ ፡ መኖሪያዬ

መሄድ ፡ መቀመጤ ፡ መቆም ፡ መነሳቴ ፡
በእጅህ አይደል ወይ መላው፡ እኔነቴ ፡ ፈጠርከኝ ፡ አኖርከኝ
እኔ ፡ ያንተ ፡ መቅደስ ፡ አንተም ፡ መኖሪያዬ
ቤቴም ፡ ያንተ ፡ ቤት ፡ ነው ፡ እጅህ ፡ አለኝታዬ ፡ ፈጠርከኝ ፡ አኖርከኝ

ሰሪዬ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ፈጣሪዬ ፡ መገኛዬ
የሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ነህ ፡ መኖሪያዬ