From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
አስራት ፡ ሙላቸው (Asrat Mulachew)
|
|
፪ (2)
|
ሕይወትህ ፡ ሕይወቴ (Hiwoteh Hiwotie)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፱ (2017)
|
ቁጥር (Track):
|
፲ ፫ (13)
|
ርዝመት (Len.):
|
8:11
|
ጸሐፊ (Writer):
|
አስራት (Asrat M.Property "Writer" has been marked for restricted use. )
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የአስራት ፡ ሙላቸው ፡ አልበሞች (Albums by Asrat Mulachew)
|
|
ፈውሴ ለነፍሴ በመመለሴ እንደሆነ አውቄያለሁ - መልሰኝ እመለሳለሁ
መልሰኝ መልሰኝ መልሰኝ እመለሳለሁ
ፈውሰኝ ፈውሰኝ ፈውሰኝ ድኜ ቀራለሁ
እርኩሰት አብዝተን በደል ጨምረናል
አመጽን በመዝሙር በጩኸት ከድነናል - ማረን ይቅር በለን
ተመለሱ የሚል ምክርህን ንቀናል
ልዑሉ በሰማይ መኖርህን ረስተናል - ማረን ይቅር በለን
አቤቱ አድነን እኛም እንድናለን
አቤቱ ፈውሰን እንፈወሳለን
አቤቱ አድነን እኛም እንድናለን
አቤቱ መልሰን እንመለሰላን
ኦ ማረን - ማረን ይቅር በለን /4/
ጥላቻና ትዕቢት ንቀት አስክሮናል
ይቅር ማለት ከብዶን ከምህረት ጎድለና - ማረን ይቅር በለን
ፍሬ ሳናፈራ እንባ ማብዛታችን
ከቶ አልጠቀመንም ግብዝነታችን - ማረን ይቅር በለን
ጎራ እየለየን ውጊያ ሰልጥነናል
ክቡር ደምህን ረግጠን ወንድምን ገድለናል - ማረን ይቅር በለን
የሰጠኸን ገንዘብ ጌታ ሆኖብናል
በኢየሱስ ስም እያልን ነፍስን አሳደናል - ማረን ይቅር በለን
ማጉረምረምን ትተን ስለቅጣታችን
ወዳንተ እንመለስ ይቅር መንገዳችን - ማረን ይቅር በለን
ወደላይ ይነሳ ልባችን ከእጃችን
ደመናትን ይለፍ ይሂድ ልመናችን - ማረን ይቅር በለን
መሪር ሃዘን ሊሆን ኢካቦድ ተወልዶ
ካንተ ፊት ሲጠፋ ሰው ሃጢያት ተላምዶ - - ማረን ይቅር በለን
እያየን ሲርቀን ክብርህ ከፊታችን
ዛሬ ላይ መልሰን አንተው ነህ ተስፋችን - - ማረን ይቅር በለን
|