እገዛልሃለሁ (Egezalehalew) - አስራት ፡ ሙላቸው

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አስራት ፡ ሙላቸው
(Asrat Mulachew)

Asrat Mulachew 2.jpg


(2)

ሕይወትህ ፡ ሕይወቴ
(Hiwoteh Hiwotie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፱ (2017)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:09
ጸሐፊ (Writer): አስራት
(Asrat M.
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስራት ፡ ሙላቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Asrat Mulachew)

ይገባሃል መሰጠቴ አክብሮቴ መገዛቴ
ይገባሃል ማንነቴ ይህ ህይወቴ
እራስህን ለኔ ሰጠህ - ቅድስና ባህሪህ ነው
(ኔም ላንተ ሆ) እኔም ላንተ እቀደሳለሁ

                እገዛልሃለሁ /4/ ሁሌ አመልክሃለሁ /2/

አባት እያልኩህ ክብር አልነፍግህም
ጌታ እያልኩህ አላዋርድህም
በከንፈር ብቻ አለሁ እያልኩኝ
በራቀህ ልቤ አላመልክህም

               እገዛልሃለሁ /4/ ሁሌ አመልክሃለሁ /2/

አባት ነህና ያባትነትክን መገዛት
ጌታ ነህና የሚገባህን መፈራት
እሰጥሃለሁ አመልክሃለሁ ከፍፁም ልቤ
ያንተ መክበር ነው ጥማት ረሃቤ

              እገዛልሃለሁ /4/ ሁሌ አመልክሃለሁ /2/


ላመልክህ እወዳለሁ ክብሬን ልጥልልህ
አንተን ማመስገኔ ክብር ነው ለእኔ

             እገዛልሃለሁ /4/ ሁሌ አመልክሃለሁ /2/